Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 35:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህም በኋላ ሌዋውያኑ ለራሳቸውና የአሮን ዘሮች ለሆኑት ካህናት የፋሲካን መሥዋዕት አዘጋጁ፤ ይህንንም ያደረጉት ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን በሙሉ ለማቃጠል እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ስለ ነበር ነው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚህ በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱ ዝግጅት አደረጉ፤ ምክንያቱም ካህናቱ የአሮን ልጆች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሥቡን እስከ ሌሊት ድረስ ያቀርቡ ስለ ነበር ነው። ስለዚህ ሌዋውያኑ ለራሳቸውና ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ዝግጅት አደረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከዚያም በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱ አዘጋጁ፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን ለማቅረብ እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ነበርና ስለዚህ ሌዋውያን ለራሳቸውና ለአሮን ልጆች ለካህናቱ አዘጋጁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከዚ​ያም በኋላ ለራ​ሳ​ቸ​ውና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ላሉ ለካ​ህ​ናቱ አዘ​ጋጁ፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስቡን ለማ​ቅ​ረብ እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ሌዋ​ው​ያን ለራ​ሳ​ቸ​ውና ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ አዘ​ጋጁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከዚያም በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱ አዘጋጁ፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን ለማቅረብ እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ነበርና ስለዚህ ሌዋውያን ለራሳቸውና ለአሮን ልጆች ለካህናቱ አዘጋጁ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 35:14
5 交叉引用  

ሌዋውያኑም በሕጉ መሠረት የፋሲካውን መሥዋዕት በእሳት ጠበሱት፤ የተቀደሰውንም ቊርባን በምንቸት፥ በሰታቴና በድስት ቀቅለው ሥጋውን በፍጥነት ለሕዝቡ አከፋፈሉ፤


ከዚህ በታች ስማቸው የተመለከተው የሌዋዊው የአሳፍ ጐሣ የሆኑ መዘምራንም ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት፥ በተመደበላቸው ስፍራ ነበሩ፤ እነርሱም አሳፍ፥ ሄማንና የንጉሡ ነቢይ ይዱታን ናቸው፤ ሌሎች ሌዋውያን የፋሲካውን መሥዋዕት ያዘጋጁላቸው ስለ ነበር፥ የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎች ስፍራቸውን አይተዉም ነበር፤


ሠራተኞቹ የቤተ መቅደሱን መሠረት ማኖር በጀመሩበት ጊዜ ካህናቱ ልብሰ ተክህኖአቸውን ለብሰው በእጃቸው እምቢልታ በመያዝ የአሳፍ ቤተሰብ ተወላጆች የሆኑ ሌዋውያንም ጸናጽል ይዘው በረድፍ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ከንጉሥ ዳዊት ዘመን ጀምሮ ተያይዞ በመጣው መመሪያ መሠረት በመዝሙር እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ በሥርዓቱ መሠረት ራሳቸውን አነጹ፤ ሌዋውያኑም በፋሲካው በዓል አከባበር ላይ ከምርኮ ለተመለሱት ሕዝብና ለካህናቱ፥ እንዲሁም ለራሳቸው የቀረቡትን እንስሶች ዐረዱ።


跟着我们:

广告


广告