Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 35:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረቡትን እንስሶች በየቤተሰቡ ለተመደበው ሕዝብ አከፋፈሉ፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት በኦሪት ሕግ በተሰጠው መመሪያ መሠረት መሥዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ ነው፤ እንዲሁም በበሬዎቹ አደረጉ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈው ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡም፣ እንደየቤተ ሰቡና እንደየምድቡ ለሕዝቡ ለመስጠት የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለዩ፤ ወይፈኖቹንም እንደዚሁ አደረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በሙሴም መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ለጌታ እንዲያቀርቡ በየአባቶቻቸው ቤቶች ለሕዝቡ ልጆች እንዲሰጡ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለዩ። እንዲሁም በበሬዎቹ አደረጉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻፈ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ርቡ ዘንድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እንደ ክፍ​ላ​ቸው ለሕ​ዝቡ ልጆች እን​ዲ​ሰጡ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለዩ። እን​ዲ​ሁም በበ​ሬ​ዎቹ አደ​ረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በሙሴም መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ በየአባቶቻቸው ቤቶች ለሕዝቡ ልጆች እንዲሰጡ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለዩ። እንዲሁም በበሬዎቹ አደረጉ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 35:12
9 交叉引用  

ለፋሲካውም በዓል የታረዱትን የበግና የፍየል ጠቦቶች ሌዋውያኑ ቆዳቸውን ገፈፉአቸው፤ ካህናቱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ረጩ፤


ሌዋውያኑም በሕጉ መሠረት የፋሲካውን መሥዋዕት በእሳት ጠበሱት፤ የተቀደሰውንም ቊርባን በምንቸት፥ በሰታቴና በድስት ቀቅለው ሥጋውን በፍጥነት ለሕዝቡ አከፋፈሉ፤


ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው።


ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው መባ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡት ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነው ስብ በሙሉ፥


ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በመሆኑ የአሮን ልጆች በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠዊያ ላይ ያቃጥሉት፤ ይህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው።


የምግብ ቊርባን አድርጋችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ይኸውም ነውር የሌለባቸው ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤


ይህን ሁሉ መሥዋዕትና የመጠጥ መባ በቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቊርባን ጋር ተጨማሪ በማድረግ ታቀርባላችሁ፤ እንስሶቹም ነውር የሌለባቸው መሆናቸውን አረጋግጡ።


跟着我们:

广告


广告