Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 34:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ከዚህ በኋላ መላው የብንያም ሕዝብና በኢየሩሳሌም የተገኙ ሌሎች ሰዎች ሁሉ ቃል ኪዳኑን ይጠብቁ ዘንድ ቃል እንዲገቡ አደረገ፤ በዚህም መሠረት የኢየሩሳሌም ሕዝብ ከቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር የገቡት ቃል ኪዳን የሚጠይቀውን ግዴታ ሁሉ ፈጸሙ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከዚህ በኋላ በኢየሩሳሌምና በብንያም የሚኖረው ሁሉ በዚህ ነገር ቃል እንዲገባ አደረገ፤ የኢየሩሳሌምም ሕዝብ የአባቶቹ አምላክ ባዘዘው የአምላክ ቃል ኪዳን መሠረት ፈጸሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 በኢየሩሳሌምና በብንያምም የተገኙትን ሁሉ በዚህ ነገር አማለ፤ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት የአባቶቻቸው አምላክ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን እንደሚያዝዘው አደረጉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በብ​ን​ያ​ምም ሀገር የተ​ገ​ኙ​ትን ሁሉ በዚህ ነገር አማለ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 በኢየሩሳሌምና በብንያምም የተገኙትን ሁሉ በዚህ ነገር አማለ፤ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት የአባቶቻቸው አምላክ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን እንዳዘዘ አደረጉ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 34:32
11 交叉引用  

ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።”


አሳ የይሁዳ ሰዎች የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲፈጽሙ፥ ሕጉንና ትእዛዞቹን እንዲጠብቁ አዘዘ፤


የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ያመልኩትም ዘንድ በመስማማት ቃል ኪዳን ገቡ፤


መሥዋዕቱን የማቅረብ ሥራ በተፈጸመ ጊዜ ንጉሥ ሕዝቅያስና በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ።


ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የንጉሡንና የባለሥልጣኖቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ ልብ አነሣሣ።


የእግዚአብሔርንም መሠዊያ በማደስ በላዩ ላይ የኅብረት መሥዋዕትና የምስጋና መባን አቀረበ፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያመልኩም ዘንድ መላውን የይሁዳ ሕዝብ አዘዘ።


ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሐሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ።


ንጉሥ ኢዮስያስ በእስራኤል ግዛት ውስጥ የነበሩትን አጸያፊ ጣዖቶች ሁሉ አስወግዶ፥ ሕዝቡ አምላኩን እግዚአብሔርን እንዲያገለግል አደረገ፤ በዘመነ መንግሥቱም ሁሉ ሕዝቡ ከቀድሞ አባቶቹ አምላክ ከእግዚአብሔር ፈቀቅ አላሉም።


አሁን እንግዲህ እነዚህን ባዕዳን ሴቶች ከነልጆቻቸው ማሰናበት እንደሚገባን ለአምላካችን ቃል እንግባ፤ አንተ ጌታዬና የአምላካችንን ትእዛዝ የሚያከብሩ ሌሎችም የምትሰጡንን ምክር ሁሉ እንፈጽማለን፤ የእግዚአብሔር ሕግ የሚያዘውን ሁሉ እናደርጋለን፤


ለንጉሡ እታዘዛለሁ ብለህ በመሐላ ለእግዚአብሔር ቃል ስለ ገባህ ለንጉሥ ታማኝ ሁን።


ይህን ሁሉ ከፈጸመች በኋላ እምነት የማይጣልባት የእስራኤል እኅት የሆነችው ይሁዳ፥ እንደገና ወደ እኔ ለመመለስ የምትሞክር መስላ የታየችው ከልብዋ ሳይሆን ከአንገት በላይ ነበር፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


跟着我们:

广告


广告