Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 34:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሌሎቹ ሌዋውያን ዕቃዎችን ለሚያጓጒዙና በልዩ ልዩ ሥራ ለተመደቡ ሠራተኞች የበላይ ኀላፊዎችና ተቈጣጣሪዎች ሲሆኑ፥ የቀሩት ሌዋውያን ደግሞ ጸሐፊዎች ወይም ዘብ ጠባቂዎች ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የጕልበት ሠራተኞች ኀላፊ በመሆን፣ በየሥራው ላይ የተመደቡትን ሠራተኞች ይቈጣጠሩ ነበር። ጥቂቶቹ ሌዋውያን ደግሞ ኀላፊዎች፣ ጸሓፊዎችና በር ጠባቂዎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በተሸካሚዎችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚሠሩ ላይ ተሾመው ነበር፤ ጸሐፊዎቹና አለቆቹም የደጁም ጠባቂዎች ከሌዋውያን ወገን ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በተ​ሸ​ካ​ሚ​ዎ​ችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚ​ሠሩ ላይ ተሾ​መው ነበር፤ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቹና አለ​ቆ​ቹም በረ​ኞ​ቹም ከሌ​ዋ​ው​ያን ወገን ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በተሸካሚዎችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚሠሩ ላይ ተሾመው ነበር፤ ጸሐፊዎቹና አለቆቹ፥ በረኞቹም ከሌዋውያን ወገን ነበሩ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 34:13
17 交叉引用  

ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።


እነርሱንም እንዲረዱ የይዱቱን ልጅ ዖቤድኤዶምና ከእርሱ ጐሣ ሌሎች ሥልሳ ስምንት ሰዎች ተመደቡ፤ የይዱቱን ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖሳ ለቅጽር በሮቹ ጥበቃ ኀላፊዎች ሆኑ።


ሄማንና ይዱታን ለእምቢልታዎች፥ ለጸናጽሎችና የምስጋና መዝሙር ሲዘመር ለሚጠቀሙባቸው ሌሎች የዜማ ዕቃዎች ኀላፊዎች ሆኑ፤ የይዱቱን ልጆች አባሎች ለቅጽር በሮች ጥበቃ ኀላፊዎች ሆኑ።


በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የቤተ መቅደስ ዘበኞች የሚከተሉት ናቸው፦ ሻሉም፥ ዓቁብ፥ ጣልሞን፥ አሒማንና ወንድሞቻቸው፤ የእነርሱም አለቃ ሻሉም ነበር፤


በመንፈሳዊ ጉዳይ ሁሉ ወሳኝ ሥልጣን የሚኖረው ሊቀ ካህናቱ አማርያ ነው፤ በሌላው ጉዳይ ሁሉ ወሳኝ ሥልጣን የሚኖረው የይሁዳ አስተዳዳሪ የሆነው የእስማኤል ልጅ ዘባድያ ነው፤ ሌዋውያን በፊታችሁ እንደ ባለሥልጣን ሆነው ያገለግላሉ፤ ያለ ፍርሀት በድፍረት ሥሩ! እግዚአብሔርም መልካም ሥራ ከሚሠሩት ጋር ይሁን!”


እንጨት ለሚቈርጡ ለሠራተኞችህ ስንቅ የሚሆን ሁለት ሚሊዮን ኪሎ ስንዴ፥ ሁለት ሚሊዮን ኪሎ ገብስ፥ አራት መቶ ሺህ ሊትር የወይን ጠጅና አራት መቶ ሺህ ሊትር የወይራ ዘይት እልክልሃለሁ።”


ከእነርሱም መካከል ሰባው ሺህ ዕቃ እንዲያጓጒዙ፥ ሰማኒያው ሺህ በተራራዎች ላይ ድንጋይ እንዲፈልጡ አደረገ፤ ደግሞም ሥራው በትክክል መካሄዱን የሚቈጣጠሩ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎችን ሾመ።


ሰሎሞን ለሚያከናውነው ልዩ ልዩ የሕንጻ ሥራ፥ የጒልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ገባሮች ሁለት መቶ ኀምሳ እስራኤላውያን ኀላፊዎች ነበሩአቸው።


አባቱ ዳዊት የደነገጋቸውን መመሪያዎች በመከተልም የካህናቱንና ካህናቱን በሥራና መዝሙር በመዘመር የሚረዱትን ሌዋውያን የየዕለቱን የሥራ መደብ አቀናበረ፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የቤተ መቅደሱ ዘበኞች በእያንዳንዱ ቅጽር በር የዕለት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አከፋፍሎ መደበ።


በዚህ ጊዜ የይሁዳ ሰዎች “የሸክም ሥራ እያደከመን ሄደ፤ ገና መነሣት ያለበት ፍርስራሽ ብዙ ነው፤ ቅጽሩን እንሠራ ዘንድ አንችልም” አሉ።


ታዲያ ‘እኛ ጠቢባን ነን፤ የእግዚአብሔርንም ሕግ እናውቃለን’ የምትሉት ስለምንድን ነው? ሐሰተኞች ጸሐፊዎች ሕጌን እንዳዛቡ አትመለከቱምን?


በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች በካህናት አለቃው ግቢ ተሰበሰቡ።


跟着我们:

广告


广告