Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 34:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አናጢዎቹና ግንበኞቹም ሥራውን በታማኝነት አከናወኑ፤ የእነርሱም የበላይ ተቈጣጣሪዎች ከመራሪ ጐሣ ያሐትና አብድዩ፥ ከቀዓት ጐሣ ዘካርያስና መሹላም ተብለው የሚጠሩት አራት ሌዋውያን ነበሩ፤ (ሌዋውያን ሁሉ በዜማ መሣሪያ የመዘመር ከፍ ያለ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ነበሩ፤)

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሰዎቹም ሥራውን በታማኝነት አከናወኑ። የበላይ ሆነው አመራር የሚሰጧቸውም ከሜራሪ ጐሣ የሆኑት ሌዋውያን፣ ኢኤትና አብድዩ፣ ከቀዓት ጐሣ ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። በዜማ ዕቃ የላቀ ችሎታ የነበራቸው ሌዋውያን ሁሉ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰዎቹም ሥራውን በታማኝነት ሠሩ፤ በእነርሱም ላይ የተሾሙት፥ ሥራውንም የሚሠሩት ሌዋውያን ከሜራሪ ልጆች ኢኤትና አብድዩ፥ ከቀዓትም ልጆች ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። ከሌዋውያንም ወገን በዜማ ዕቃ አዋቂዎች የነበሩ ሁሉ

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሰዎ​ቹም ሥራ​ውን በመ​ታ​መን አደ​ረጉ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የተ​ሾ​ሙት፥ ሥራ​ው​ንም የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሌዋ​ው​ያን ከሜ​ራሪ ልጆች ይኤ​ትና አብ​ድ​ያስ፥ ከቀ​ዓ​ትም ልጆች ዘካ​ር​ያ​ስና ሜሱ​ላም ነበሩ። ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገን በዜማ ዕቃ ዐዋ​ቂ​ዎች፥ የነ​በሩ ሁሉ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሰዎቹም ሥራውን በመታመን አደረጉ፤ በእነርሱም ላይ የተሾሙት፥ ሥራውንም የሚሠሩት ሌዋውያን ከሜራሪ ልጆች ኢኤትና አብድዩ፥ ከቀዓትም ልጆች ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። ከሌዋውያንም ወገን በዜማ ዕቃ አዋቂዎች የነበሩ ሁሉ

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 34:12
15 交叉引用  

የሌዊ ልጆች፦ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ ናቸው።


ለሥራው ኀላፊነት የተመረጡትም ሰዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ነበሩ ገንዘቡን የሰጡአቸውን ሰዎች አይቈጣጠሩአቸውም ነበር።


የሥራው ኀላፊዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ሆኑ እነርሱን ስለ ገንዘቡ አወጣጥ መቈጣጠር አያስፈልግም።”


በዚያም ከእነርሱ ጋር ሄማን፥ ይዱታን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ ፍቅር በማሰብ ዘወትር ለእርሱ የምስጋና መዝሙር ያቀርቡ ዘንድ ሌሎችም በተለይ የተመረጡ ሰዎች ነበሩ፤


አራት ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ለዘብ ጥበቃ ተመደቡ፤ ሌሎች አራት ሺህ ደግሞ ንጉሡ በሚሰጣቸው የሙዚቃ መሣሪያ እግዚአብሔርን በዝማሬ ለማመስገን ተመደቡ።


ዐሥራቱንና በኲራቱን፥ የተቀደሱትንም ስጦታዎች ሁሉ በእምነት ወደዚያ አስገቡ፤ ኮናንያ ተብሎ የሚጠራው ሌዋዊ የዕቃ ግምጃ ቤቱ ኀላፊ ሆኖ ሲሾም፥ ወንድሙ ሺምዒ ደግሞ ረዳቱ ሆኖ ተሾመ፤


ሌዋዊው ኢያሱና ወንዶች ልጆቹ፥ እንዲሁም ዘመዶቹ፥ ቃድሚኤልና ከሖዳዊያ ቤተሰብ ወገን የሆኑ ወንዶች ልጆቹም ሁሉ በአንድነት ተባብረው ቤተ መቅደሱን እንደገና የመሥራቱን ኀላፊነት ተረከቡ፤ የሔናዳድ ዘሮች የሆኑት ሌዋውያንም ይረዱአቸው ነበር።


እኔም የኢየሩሳሌምን ከተማ ያስተዳድሩ ዘንድ ሁለት ሰዎችን ሾምኩ፤ እነርሱም የእኔ ወንድም የሆነው ሐናኒና የምሽግ ኀላፊ የነበረው ሐናንያ ናቸው፤ ሐናንያ እውነተኛና እግዚአብሔርን በመፍራት ረገድ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሰው ነበር።


ታማኝ ሰው የተባረከ ሕይወት ይኖረዋል፤ ሀብታም ለመሆን የሚስገበገብ ሰው ግን ቅጣት ያገኘዋል።


የዓምራም፥ የይጽሃር፥ የኬብሮንና የዑዚኤል ቤተሰቦች በቀዓት ጐሣ ውስጥ ተጠቃለው ነበር፤


ባለ ዐደራዎችም ታማኞች ሆነው መገኘት አለባቸው።


跟着我们:

广告


广告