Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 33:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አባቱ እንዳደረገው ሁሉ ራሱን በትሕትና ዝቅ አድርጎ በማዋረድ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤ እንዲያውም ከአባቱ ይበልጥ የከፋ ኃጢአት ሠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አሞን በእግዚአብሔር ፊት ራሱን እንዳዋረደ እንደ አባቱ እንደ ምናሴ ራሱን አላዋረደም፤ ነገር ግን በበደል ላይ በደል እየጨመረ ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አባቱም ምናሴ በጌታ ፊት ራሱን እንዳዋረደ እንዲሁ እርሱ ራሱን አላዋረደም፤ ነገር ግን አሞጽ መተላለፉን እጅግ አበዛ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ፈጽሜ በደ​ልሁ፤ ኀጢ​አ​ቴ​ንም አም​ና​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አባቱም ምናሴ ሰውነቱን እንዳዋረደ በእግዚአብሔር ፊት ሰውነቱን አላዋረደም፤ ነገር ግን አሞን መተላለፉን እጅግ አበዛ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 33:23
9 交叉引用  

አካዝ፥ ችግሩ እየባሰበት በሄደ ጊዜ ከምንጊዜውም ይበልጥ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ።


ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤


ምናሴ ሥቃይ በበዛበት ጊዜ ራሱን በትሕትና በማዋረድ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ፤ የእግዚአብሔርንም ርዳታ ለመነ፤


ንጉሥ ምናሴ ወደ እግዚአብሔር ያቀረበው ጸሎትና፥ እግዚአብሔርም ለጸሎቱ የሰጠው መልስ፥ ተጸጽቶ ንስሓ ከመግባቱ በፊት ያደረገው ኃጢአት ሁሉ፥ ማለትም የፈጸመው ልዩ ልዩ ክፋት፥ እርሱ ራሱ የሠራቸው የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችና አሼራ ተብላ የምትጠራው ሴት አምላክ ምስሎች፥ ያመልካቸው የነበሩ ጣዖቶች ሁሉ፥ በነቢያት የታሪክ መጻሕፍት ውስጥ ተመዝግበው ይገኛሉ።


እርሱም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገረውን ነቢዩን ኤርምያስን በትሕትና አላዳመጠውም።


ነገር ግን ያዳመጠኝም ሆነ ለትእዛዜ ትኲረት የሰጠ ሰው አልነበረም፤ ይልቁንም ከቀድሞ አባቶቻችሁ ብሳችሁ እልኸኞችና ዐመፀኞች ሆናችሁ።”


ሕዝቤ ሆይ! ይህን ሁሉ አጸያፊ ነገር ስታደርጉ ጥቂት ኀፍረት ተሰምቶአችሁ ነበርን? ኀፍረት ሊሰማችሁ ቀርቶ ዐይናችሁ እንኳ ሰበር አላለም፤ ስለዚህ ሌሎች እንደ ወደቁ እናንተም ትወድቃላችሁ፤ እኔ በምቀጣችሁ ጊዜ ፍጻሜአችሁ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


“አንተም ብልጣሶር የእርሱ ልጅ በመሆንህ ይህን ሁሉ ስታውቅ ራስህን ዝቅ በማድረግ ትሕትና አላሳየህም።


ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አስመሳዮች ግን ሰዎችን እያሳሳቱና ራሳቸውም እየተሳሳቱ፥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤


跟着我们:

广告


广告