Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 33:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ምናሴ ሞተ፤ በቤተ መንግሥቱም አጠገብ በሚገኘው ስፍራ ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሞን ነገሠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ምናሴም እንደ አባቶቹ ሁሉ አንቀላፋ፤ በቤተ መንግሥቱም ተቀበረ። ልጁም አሞን በርሱ ፈንታ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በቤቱም ቀበሩት፤ ልጁም አሞጽ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ቍጥሩ ከባ​ሕር አሸዋ የሚ​በ​ልጥ በደ​ልን በድ​ያ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ቴም ብዙ ነውና፤ ከበ​ደ​ሌም ብዛት የተ​ነሣ ቀና ብዬ የሰ​ማ​ይን ርዝ​መት አይ ዘንድ አገ​ባቤ አይ​ደ​ለም። ሰው​ነ​ቴን ከኀ​ጢ​አቴ አሳ​ር​ፋት ዘንድ በብ​ረት ቀፎ ደከ​ምሁ፤ በዚ​ህም ደግሞ አላ​ረ​ፍ​ሁም፤ መዓ​ት​ህን አነ​ሣ​ሥ​ቻ​ለ​ሁና፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቤቱም ቀበሩት፤ ልጁም አሞን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 33:20
9 交叉引用  

አሞንና ኢዮስያስ፤


ኢዮራም በሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ስምንት ዓመት ገዛ፤ እርሱ በሞተ ጊዜ ማንም አላዘነለትም፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም።


ሕዝቅያስ ሞተ፤ በላይኛው ክፍል በሚገኘውም በዳዊት ልጆች መካነ መቃብር ተቀበረ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብም ሁሉ ታላቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት አደረጉለት፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ምናሴ ነገሠ።


ንጉሥ ምናሴ ወደ እግዚአብሔር ያቀረበው ጸሎትና፥ እግዚአብሔርም ለጸሎቱ የሰጠው መልስ፥ ተጸጽቶ ንስሓ ከመግባቱ በፊት ያደረገው ኃጢአት ሁሉ፥ ማለትም የፈጸመው ልዩ ልዩ ክፋት፥ እርሱ ራሱ የሠራቸው የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችና አሼራ ተብላ የምትጠራው ሴት አምላክ ምስሎች፥ ያመልካቸው የነበሩ ጣዖቶች ሁሉ፥ በነቢያት የታሪክ መጻሕፍት ውስጥ ተመዝግበው ይገኛሉ።


አሞን ዕድሜው ኻያ ሁለት ዓመት ሲሆነው በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሁለት ዓመት ገዛ፤


ሶፎንያስ የኩሺ ልጅ ሲሆን፥ ኩሺ የገዳልያ ልጅ፥ ገዳልያ የአማርያ ልጅ፥ አማርያ ደግሞ የንጉሥ ሕዝቅያስ ልጅ ነው፤ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን እግዚአብሔር ለሰፎንያስ የተናገረው ትንቢት እንደሚከተለው ነው።


ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤ ምናሴ አሞጽን ወለደ፤ አሞጽ ኢዮስያስን ወለደ፤


ሳሙኤል ሞተ፤ መላው እስራኤላውያንም በአንድነት መጥተው አለቀሱለት፤ ከዚያም በኋላ በራማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ቀበሩት። ከዚያም በኋላ ዳዊት ወደ ፋራን ምድረ በዳ ሄደ፤


跟着我们:

广告


广告