Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 33:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሕዝቡ በሌሎቹ ኰረብታማ የማምለኪያ ስፍራዎች ላይ መሥዋዕት ማቅረባቸውን ቢቀጥሉም እንኳ መሥዋዕቱን የሚያቀርቡት ለእግዚአብሔር ብቻ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሕዝቡ ግን በኰረብታ መስገጃ ስፍራዎች መሠዋቱን ቢቀጥልም፣ የሚሠዋው ግን ለአንዱ አምላክ ለእግዚአብሔር ብቻ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሕዝቡ ግን ገና በኮረብታው መስገጃዎች ይሠዋ ነበር፤ ቢሆንም ግን እንዲህ የሚያደርገው ለአምላኩ ለጌታ ብቻ ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ለክ​ብ​ርህ ከፍ​ተ​ኛ​ነት ፍጻሜ የለ​ው​ምና፥ የቍ​ጣ​ህም መቅ​ሠ​ፍት በኃ​ጥ​አን ላይ ግሩም ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ሕዝቡ ግን ገና በኮረብታው መስገጃዎች ይሠዋ ነበር፤ ቢሆንም ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ብቻ ነበረ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 33:17
6 交叉引用  

ኢዮሣፍጥ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ አሳ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ሠራ፤ ይሁን እንጂ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን አልደመሰሰም ነበር፤ ስለዚህም ሕዝቡ በእነዚያ ቦታዎች መሥዋዕት ማቅረብና ዕጣን የማጠን ተግባሩን አልተወም ነበር፤


ነገር ግን በየኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብን የማምለኪያ ቦታዎች አልደመሰሰም፤ ስለዚህም ሕዝቡ በየኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤


ምንም እንኳ አሳ በኰረብቶቹ ላይ የነበሩትን የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ ባይደመስሳቸው፥ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነ፤


ነገር ግን በከፍተኛ ቦታዎች ላይ የሚገኙትን የማምለኪያ ቦታዎች አላስወገደም፤ ሕዝቡም ወደ ቀድሞ አባቶቹ አምላክ ወደ እግዚአብሔር በሙሉ ልቡ ገና አልተመለሰም ነበር።


ከዚህ ቀደም የተቀደሱትን የእግዚአብሔርን ማምለኪያ ስፍራዎችና መሠዊያዎችን ያፈራረሰ፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብም በአንድ መሠዊያ ላይ ብቻ ዕጣን እያጠነ እንዲሰግድ ያደረገ ሕዝቅያስ ነው፤


ምናሴ ያደረገው ሌላ ነገር ሁሉ፥ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ያቀረበው ጸሎት፥ ነቢያት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ለምናሴ የተናገሩአቸው ቃላት ጭምር፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ይገኛሉ።


跟着我们:

广告


广告