Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 32:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የአሦር ንጉሠ ነገሥት የጻፈው ደብዳቤ “የሌሎች ሕዝቦች አማልክት ሕዝቦቻቸውን ከእኔ እጅ አላዳኑም፤ የሕዝቅያስም አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊያድናቸው ከቶ አይችልም” በማለት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚዘልፍ ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ንጉሡም እንደዚሁ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በመሳደብ፣ “የሌሎቹ አገሮች ሕዝቦች አማልክት፣ ከእጄ እንዳልታደጉ ሁሉ፣ የሕዝቅያስም አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊታደግ አይችልም” ሲል በርሱ ላይ ደብዳቤ ጻፈ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ደግሞም የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመስደብ፥ በእርሱም ላይ ለመናገር፦ “የምድር አሕዛብ አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ ለማዳን እንዳልቻሉ፥ እንዲሁ የሕዝቅያስ አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊያድን አይችልም” የሚል ደብዳቤ ጻፈ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ደግ​ሞም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እየ​ተ​ገ​ዳ​ደረ በእ​ር​ሱም ላይ እየ​ተ​ና​ገረ፥ “የም​ድር አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሕዝ​ባ​ቸ​ውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ እን​ዳ​ል​ቻሉ፥ እን​ዲሁ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ አም​ላክ ሕዝ​ቡን ከእጄ ያድን ዘንድ አይ​ች​ልም” የሚል ደብ​ዳቤ ጻፈ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ደግሞም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመስደብ፥ በእርሱም ላይ ለመናገር “የምድር አሕዛብ አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ እንዳልቻሉ፥ እንዲሁ የሕዝቅያስ አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ያድን ዘንድ አይችልም” የሚል ደብዳቤ ጻፈ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 32:17
16 交叉引用  

የአሦር ነገሥታት አገሮችን ሁሉ እንዴት ፈጽመው እንደ ደመሰሱ ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?


የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዔዴንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን?


ንጉሥ ሕዝቅያስ ደብዳቤውን ከመልክተኞች ተቀብሎ አነበበው፤ ወደ ቤተ መቅደስም ወስዶ ደብዳቤውን በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው፤


የሰደብከውና የተዳፈርከው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? በትዕቢትስ ዐይንህን ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ ነው።


በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”


በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፦


አባቶቼ ካወደሙአቸው ከእነዚህ አገሮች አማልክት መካከል አንዱ እንኳ አገሩን ያዳነበት ጊዜ አለን? ታዲያ፥ የእናንተ አምላክ ከእጄ እንዴት ሊያድናችሁ ይችላል?


የአሦር ባለሥልጣኖችም በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሕዝቅያስ ላይ ከዚህ የከፋ ነገር ተናገሩ፤


ከዚህም በኋላ ሰንባላጥ ከአገልጋዮቹ አንዱን ለአምስተኛ ጊዜ መልእክት አስይዞ ወደ እኔ ላከ፤ የተላከውም ግልጥ ደብዳቤ እንዲህ የሚል ነበር፦


መጥረቢያ እንጨት በሚቈርጥበት በባለቤቱ ላይ መነሣት ይችላልን? መጋዝስ በሚሰነጥቅበት ሰው ላይ መነሣት ይችላልን? እንዲሁም በትር በሚይዘው ሰው ላይ ኀይል አይኖረውም።


ንጉሥ ሕዝቅያስ ደብዳቤውን ከመልእክተኞቹ እጅ ተቀብሎ አነበበው፤ ወደ ቤተ መቅደስም ወስዶ ደብዳቤውን በእግዚአብሔር ፊት በማቅረብ፥


እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔርን ስም፥ መኖሪያውንና በሰማይ የሚኖሩትን መሳደብ ጀመረ።


ዳዊትም በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እስራኤልን ከዚህ አሳፋሪ ውርደት ለሚያድን ሰው ምን ይደረግለታል? ኧረ ለመሆኑ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት የሚፈታተን ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ።


እኔ ያንተ አሽከር አንበሳና ድብ ገድያለሁ፤ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ስለ ተፈታተነ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告