Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 32:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አባቶቼ ካወደሙአቸው ከእነዚህ አገሮች አማልክት መካከል አንዱ እንኳ አገሩን ያዳነበት ጊዜ አለን? ታዲያ፥ የእናንተ አምላክ ከእጄ እንዴት ሊያድናችሁ ይችላል?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አባቶቼ ሙሉ በሙሉ ከደመሰሷቸው ከእነዚህ መንግሥታት አማልክት ሁሉ፣ ሕዝቡን ከእጄ ሊያድን የቻለ አምላክ የትኛው ነው? ታዲያ አምላካችሁ እንዴት ከእጄ ሊታደጋችሁ ይችላል?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አባቶቼ ካጠፉአቸው ከአሕዛብ አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄ ለማዳን የቻለ ማንስ ነበር፤ እናንተንስ አምላካችሁ ከእጄ ለማዳን የሚችል ይመስላችኋልን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አም​ላ​ካ​ች​ሁስ ከእጄ እና​ን​ተን ለማ​ዳን ይችል ዘንድ አባ​ቶች ካጠ​ፉ​አ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሁሉ ሕዝ​ቡን ከእጄ ያድን ዘንድ የቻለ ማን ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አምላካችሁስ ከእጄ እናንተን ለማዳን ይችል ዘንድ አባቶቼ ካጠፉአቸው ከአሕዛብ አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄ ያድን ዘንድ የቻለ ማን ነው?

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 32:14
8 交叉引用  

የአሦር ንጉሠ ነገሥት የጻፈው ደብዳቤ “የሌሎች ሕዝቦች አማልክት ሕዝቦቻቸውን ከእኔ እጅ አላዳኑም፤ የሕዝቅያስም አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊያድናቸው ከቶ አይችልም” በማለት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚዘልፍ ነበር፤


እነሆ፥ ንጉሡ እስራኤላውያን በበረሓ ተዘግተው በአገሪቱ ዙሪያ የሚንከራተቱ ይመስለዋል።


ንጉሡም “ለመሆኑ እግዚአብሔር ማን ነው? የእርሱንስ ትእዛዝ ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ።


ከአሁን በፊትም ከኢየሩሳሌምና ከሰማርያ የበለጡ ጣዖቶች የሞሉባቸውን መንግሥታት አሸንፌአለሁ።


የካልኖን፥ የካርከሚሽን፥ የሐማትንና የአርፋድን ከተሞች ድል አድርጌአለሁ፤ ሰማርያንና ደማስቆንም በቊጥጥሬ ሥር አድርጌአለሁ።


“ስሜ እግዚአብሔር ነው፤ የእኔንም ክብር የሚጋራ ሌላ አምላክ የለም፤ ጣዖቶችም ምስጋናዬን እንዲካፈሉ አልፈቅድም።


跟着我们:

广告


广告