Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 31:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እነዚህ ካህናትና ሌዋውያን ራሳቸውን የቀደሱ ታማኞች ስለ ነበሩ የሚመዘገቡት ከሚስቶቻቸው ከልጆቻቸውና በእነርሱ ሥር ከሚተዳደሩት ሰዎች ሁሉ ጋር በአንድነት ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በዚህ የትውልድ መዝገብ ላይ የተዘረዘሩትን መላውን የማኅበረ ሰቡን ሕፃናት፣ ሚስቶችን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ጨመሯቸው፤ ራሳቸውን በመቀደስ ታማኞች ነበሩና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በታማኝነትም ቅድስናቸውን ጠብቀዋልና ካህነናቱ በየትውልዳቸው ከሕፃናቶቻቸውና ከሚስቶቻቸው ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻቸው እንዲሁም ከማኅበሩ ሁሉ ጋር ተቈጠሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በማ​ኅ​በ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ለተ​ቈ​ጠሩ ለሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው፥ ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ይሰጡ ነበር፤ በእ​ም​ነት ፈጽ​መው ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በማኅበሩም ሁሉ በየትውልዳቸው ለተቈጠሩ ለሕፃናቶቻቸውና ለሚስቶቻቸው ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻቸውም ይሰጡ ነበር፤ በእምነት ተቀድሰዋልና።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 31:18
6 交叉引用  

መግቢያ በሮችንና ቅጽር በሮችን ለመጠበቅ የተመረጡ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም በሚኖሩባቸው መንደሮች መሠረት ተቈጥረው ተመዘገቡ፤ የእነርሱን የቀድሞ አባቶች በዚህ ኀላፊነት የመደቡአቸው ንጉሥ ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል ነበሩ።


ካህናት በሚኖሩባቸው በሌሎች ከተሞች ቆሬን በታማኝነት የሚረዱ ዔደን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማዕያ፥ አማርያና ሸካንያ ተብለው የሚጠሩ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም በሥራቸው ምድብ መሠረት ምግቡን ወገኖቻቸው ለሆኑ ሌዋውያን በትክክል ያከፋፍሉ ነበር።


የካህናት ሥራ ምድብ በጐሣ በጐሣ ሲሆን፥ ዕድሜአቸው ኻያ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ሌዋውያን፥ የሥራ ምድብ ግን በሚያከናውኑት የሥራ ዐይነት የሚወሰን ነበር፤


ለአሮን ልጆች በተመደቡ ከተሞች ወይም የእነዚህ ከተሞች ይዞታ በሆኑት የግጦሽ ቦታዎች ከሚኖሩት ካህናት መካከል ለካህናት ቤተሰቦችና በሌዋውያን ጐሣ የስም ዝርዝር በያዘ መዝገብ ውስጥ ስማቸው ለሚገኝ ወንዶች ሁሉ ምግብን ለማከፋፈል ኀላፊዎች የሆኑ ሰዎች ነበሩ።


የሠራዊት አምላክ ግን በቅን ፍርዱ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱሱም አምላክ በእውነተኛነቱ ቅድስናውን ይገልጣል።


ይህም ጸጋ የተሰጠኝ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለአሕዛብ በማብሠር እንደ ካህን ሆኜ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል ነው፤ ስለዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰና እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ አገለግላለሁ።


跟着我们:

广告


广告