Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 31:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ካህናት በሚኖሩባቸው በሌሎች ከተሞች ቆሬን በታማኝነት የሚረዱ ዔደን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማዕያ፥ አማርያና ሸካንያ ተብለው የሚጠሩ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም በሥራቸው ምድብ መሠረት ምግቡን ወገኖቻቸው ለሆኑ ሌዋውያን በትክክል ያከፋፍሉ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ዔድን፣ ሚንያሚን፣ ኢያሱ፣ ሸማያ፣ አማርያና ሴኬንያ በካህናቱ ከተሞች ተገኝተው፣ ለካህናት ወገኖቻቸው ለታላላቆቹም ሆነ ለታናናሾቹ፣ እንደየምድባቸው፣ በማከፋፈሉ ረገድ በታማኝነት ረዱት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በካህናቱም ከተሞች ለታላላቆችና ለታናናሾች ወንድሞቻቸው በየሰሞናቸው ድርሻቸውን በታማኝነት እንዲሰጡ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማያ፥ አማርያ፥ ሴኬንያ የቆሬ ረዳቶች ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በካ​ህ​ና​ቱም ከተ​ሞች ለታ​ላ​ላ​ቆ​ችና ለታ​ና​ና​ሾች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ክፍ​ላ​ቸ​ውን በእ​ም​ነት ይሰጡ ዘንድ ኤዶም፥ ብን​ያስ፥ ኢያሱ፥ ሴሚ፥ አማ​ርያ፥ ኮክ​ን​ያስ ከእጁ በታች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በካህናቱም ከተሞች ለታላላቆችና ለታናናሾች ወንድሞቻቸው በየሰሞናቸው ክፍላቸውን በእምነት ይሰጡ ዘንድ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማያ፥ አማርያ፥ ሴኬንያ ከእጁ በታች ነበሩ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 31:15
8 交叉引用  

የእያንዳንዱ ቤተሰብ አለቃና ታናሹ እንደ ታላቁ በእኩልነት ልክ ዘመዶቻቸው የአሮን ልጆች የነበሩት ካህናት ያደርጉት በነበረው ዐይነት ለሥራቸው ምድብ ዕጣ ይጥሉ ነበር፤ ንጉሥ ዳዊት፥ ሳዶቅ፥ አቤሜሌክና የካህናትና የሌዋውያን ቤተሰቦች አለቆች ሁሉ በተገኙበት ዕጣ ተጣጥለዋል።


የሥራ ምድባቸውን ለመወሰን ወጣት ሆነ ሽማግሌ፥ አስተማሪም ሆነ ተማሪ ለማንም ልዩነት ሳይደረግ ዕጣ ይጣጣሉ ነበር።


መግቢያ በሮችንና ቅጽር በሮችን ለመጠበቅ የተመረጡ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም በሚኖሩባቸው መንደሮች መሠረት ተቈጥረው ተመዘገቡ፤ የእነርሱን የቀድሞ አባቶች በዚህ ኀላፊነት የመደቡአቸው ንጉሥ ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል ነበሩ።


ሥራውን እንዲቀጥሉ የተደረጉት ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፦ ከቀዓት ጐሣ፦ የዐማሣይ ልጅ ማሐትና የዐዛርያስ ልጅ ኢዩኤል፤ ከመራሪ ጐሣ፦ የዓብዲ ልጅ ቂሽና የይሀልኤል ልጅ ዐዛርያስ፤ ከጌርሾን ጐሣ፦ የዚማ ልጅ ዮአሕና የዮአሕ ልጅ ዔዴን፤ ከኤሊጻፋን ጐሣ፦ ሺምሪና ይዒኤል፤ ከአሳፍ ጐሣ፦ ዘካርያስና ማታንያ፤ ከሄማን ጐሣ፦ ይሒኤልና ሺምዒ፤ ከይዱቱን ጐሣ፦ ሸማዕያና ዑዚኤል።


ከእነርሱም ሥር ሆነው የሚሠሩ ይሒኤል፥ ዐዛዝያ፥ ናሐት፥ ዐሣሄል፥ ይሪሞት፥ ዮዛባድ፥ ኤሊኤል፥ ዩስማክያ፥ ማሐትና በናያ ተብለው የሚጠሩ ዐሥር ሌዋውያን ተመደቡ። እነዚህን ሁሉ የሾሙ፥ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሊቀ ካህናቱ ዐዛርያስ ናቸው፤


የቤተ መቅደሱ የምሥራቃዊ በር ዘብ ጠባቂዎች አለቃ ለነበረው ለሌዋዊው ዩምና ልጅ ለቆሬ ደግሞ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የበጎ ፈቃድ ስጦታዎች ሁሉ የመቀበልና የማከፋፈል ኀላፊነት ተሰጠው።


跟着我们:

广告


广告