Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 30:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከዳዊት ልጅ ከሰሎሞን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ይህንን የመሰለ በዓል በኢየሩሳሌም ተከብሮ ስለማያውቅ የኢየሩሳሌም ከተማ ሰዎች እጅግ ተደሰቱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰሎሞን ጊዜ አንሥቶ በኢየሩሳሌም እንዲህ ያለ በዓል ተደርጎ ስለማያውቅ፣ በኢየሩሳሌም ታላቅ ደስታ ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በኢየሩሳሌምም ታላቅ ደስታ ሆነ፤ ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰሎሞን ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ በዓል በኢየሩሳሌም አልተከበረም ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ታላቅ ደስታ ሆነ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከዳ​ዊት ልጅ ከን​ጉሥ ሰሎ​ሞን ዘመን ጀምሮ እን​ደ​ዚህ ያለ በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ተ​ደ​ረ​ገም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በኢየሩሳሌምም ታላቅ ደስታ ሆነ፤ ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰሎሞን ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ በዓል በኢየሩሳሌም አልተደረገም ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 30:26
5 交叉引用  

ንጉሡና የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ በዳዊትና በነቢዩ አሳፍ የተደረሱትን የምስጋና መዝሙሮች ለእግዚአብሔር ክብር እንዲዘምሩ ሌዋውያንን አዘዙ፤ ስለዚህ ሁሉም ተንበርክከው በመስገድ ላይ ሳሉ በታላቅ ደስታ ይዘምሩ ነበር።


ካህናቱና ሌዋውያኑም ቆመው የእግዚአብሔር በረከት በሕዝቡ ላይ እንዲወርድ ጸለዩ፤ እግዚአብሔርም በተቀደሰ መኖሪያው በሰማይ ሆኖ ጸሎታቸውን ሰማ።


ከነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ጀምሮ የፋሲካ በዓል ይህን በመሰለ ሁኔታ ከቶ ተከብሮ አያውቅም፤ ንጉሥ ኢዮስያስ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የይሁዳ፥ የእስራኤልና የኢየሩሳሌም ሕዝብ የፋሲካን በዓል አሁን ባከበሩት ዐይነት ከዚህ በፊት ከነበሩት ነገሥታት መካከል፥ አንዱ እንኳ አክብሮ አያውቅም፤


ከምርኮ ተመልሰው የመጡት ሰዎች ሁሉ ዳሶችን ሠርተው በዳሱ ውስጥ ተቀመጡ፤ ይህም ከነዌ ልጅ ኢያሱ ዘመን ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ወሰን የሌለው ደስታ ተሰምቶአቸው ነበር።


跟着我们:

广告


广告