Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 30:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በተጨማሪም ከኤፍሬም፥ ከምናሴ ከይሳኮርና ከዛብሎን ነገዶች የመጡት ብዙ ሰዎች የነጹ ስላልነበሩ የፋሲካን በዓል በሚገባ አላከበሩም፤ ንጉሥ ሕዝቅያስም ስለ እነርሱ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ምንም እንኳ ከኤፍሬም፣ ከምናሴ፣ ከይሳኮርና ከዛብሎን ከመጡት አብዛኛዎቹ ራሳቸውን ያላነጹ ቢሆንም ከተጻፈው ትእዛዝ ውጭ ፋሲካውን በሉ። ሕዝቅያስ ግን እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ቸሩ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይቅር በላቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እንደ ትእዛዙም ሳይሆን ከኤፍሬምና ከምናሴ ከይሳኮርና ከዛብሎንም ወገን እጅግ ብዙ ሰዎች ሳይነጹ ፋሲካውን በሉ። ሕዝቅያስም ስለ እነርሱ እንዲህ ብሎ ጸለየ፦ “ቸሩ ጌታ ሆይ! ሁሉንም ሰው ይቅር በል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እንደ ትእ​ዛ​ዙም ሳይ​ሆን ከኤ​ፍ​ሬ​ምና ከም​ናሴ፥ ከይ​ሳ​ኮ​ርና ከዛ​ብ​ሎ​ንም ወገን እጅግ ሰዎች ሳይ​ነጹ ፋሲ​ካ​ውን በሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እንደ ትእዛዙም ሳይሆን ከኤፍሬምና ከምናሴ ከይሳኮርና ከዛብሎንም ወገን እጅግ ሰዎች ሳይነጹ ፋሲካውን በሉ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 30:18
23 交叉引用  

ከዚያ በኋላ አብርሃም ለእግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክንና ሚስቱን፥ ሴቶች አገልጋዮቹንም ፈውሶአቸው ልጆች እንዲወልዱ አድርጎአቸዋል፤


አሁን ግን ሴቲቱን ለባልዋ መልሰህ ስጥ፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ እንዳትሞት ይጸልይልሃል፤ እርስዋን መልሰህ ባትሰጥ ግን እንደምትሞት ዕወቅ፤ አንተ ብቻ ሳትሆን ሕዝብህም በሙሉ ታልቃላችሁ።”


ስለዚህም የሀገሬን ንጉሥ በማጀብ ሪሞን የተባለ የሶርያ አምላክ ወደሚመለክበት መቅደስ ብገባና ብሰግድም እንኳ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በእርግጥም ይቅር ይለኛል።”


ይሁን እንጂ ለእግዚአብሔር ትሕትናን በማሳየት ወደ ኢየሩሳሌም ፈቃደኞች ሆነው የመጡ ከአሴር፥ ከምናሴና ከዛብሎን ነገዶች አንዳንድ ሰዎች ነበሩ፤


ስለዚህ የይሁዳ ሕዝብ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ ከሰሜን ግዛቶች የመጡ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ምድር ለዘለቄታው የሰፈሩ መጻተኞች ሁሉ እጅግ ደስ አላቸው።


ዘብ ጠባቂዎች የሆኑ ሌዋውያን በቤተ መቅደስ ውስጥ የሰበሰቡት ገንዘብ ሁሉ፥ ለሊቀ ካህናቱ ለሒልቂያ ተሰጠ፤ ገንዘቡም የተሰበሰበው ከኤፍሬም፥ ከምናሴና ከቀረውም የእስራኤል ሕዝብ፥ እንዲሁም ከይሁዳ፥ ከብንያምና ከኢየሩሳሌም ሕዝብ ነበር፤


እኔም አገልጋይህ ሆንኩ ሕዝብህ እስራኤል ፊታችንን ወደዚህ ስፍራ መልሰን ስንጸልይ ጸሎታችንን ስማ፤ መኖሪያህ በሆነው በሰማይ ስማን፤ ይቅር በለንም።


አንተ ቸር ስለ ሆንክ ቸር የሆነውን ታደርጋለህ፤ ሕጎችህን አስተምረኝ።


እግዚአብሔር ደግና ቀጥተኛ ስለ ሆነ፥ ሊከተሉት የሚገባቸውን መንገድ ለኃጢአተኞች ያስተምራል።


እግዚአብሔር ሆይ፥ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ እስከ ሰማይ፥ እውነተኛነትህም እስከ ደመና ይደርሳል።


ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ቸርና መሐሪ ነህ፤ ወደ አንተ ለሚጸልዩትም ሁሉ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ታሳያቸዋለህ።


እግዚአብሔር ሆይ! ስማን! እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር በለን! እባክህ አድምጠን! ሥራህንም ግለጥ! አምላክ ሆይ! አትዘግይ፤ ይህች ከተማና ይህ ሕዝብ በስምህ የተጠሩ ናቸው።”


ሙሴም ይህን በሰማ ጊዜ በተሰጠው መልስ ተደሰተ።


“ያልነጻና ራሱንም ያላነጻ ሰው ለማንጻት የተመደበው ውሃ በላዩ ስላልፈሰሰ የረከሰ ሆኖ ይቈያል፤ እንደዚህ ያለው ሰው የእግዚአብሔርን ድንኳን ስለሚያረክስ ከማኅበሩ ይለይ።


“እኛ በድን በመንካታችን ረክሰናል፤ ነገር ግን ከቀሩት እስራኤላውያን ተለይተን በወቅቱ ለእግዚአብሔር መባ እንዳናቀርብ ስለምን እንከለከላለን?”


ስለዚህ ማንም ሰው ይህን ኅብስት ከመብላቱና ይህንንም ጽዋ ከመጠጣቱ በፊት ራሱን መመርመር አለበት።


ማንም ሰው ወንድሙ ለሞት የማያደርስ ኃጢአት ሲሠራ ቢያየው ይጸልይለት፤ የሰውዬው ኃጢአት ለሞት የማያደርስ ከሆነ እግዚአብሔር ሕይወትን ይሰጠዋል። ነገር ግን ለሞት የሚያደርስ ኃጢአት አለ። ለእንዲህ ዐይነቱ ኃጢአት ይጸልይ አልልም።


跟着我们:

广告


广告