Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 30:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከሕዝቡ መካከል ብዙዎቹ ራሳቸውን ያላነጹ ስለ ነበሩ ለፋሲካ የሚሆኑትን የበግ ጠቦቶች ለማረድ አልተፈቀደላቸውም ነበር፤ ስለዚህ ሌዋውያን በእነርሱ ምትክ የበግ ጠቦቶቹን በማረድ ለእግዚአብሔር አቀረቡላቸው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከጉባኤው መካከል አብዛኛዎቹ ራሳቸውን ያልቀደሱ ስለ ነበሩ፣ ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ላላነጹትና ጠቦቶቻቸውን ለእግዚአብሔር መቀደስ ላልቻሉት ሁሉ የፋሲካውን በጎች ማረድ ነበረባቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በጉባኤውም ያልተቀደሱ እጅግ ሰዎች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን ለጌታ የተቀደሱ ለማድረግ ንጹሐን ላልሆኑት ሁሉ የፋሲካውን ጠቦት ያርዱላቸው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በጉ​ባ​ኤ​ውም ያል​ነጹ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሳ​ቸ​ውን ላላ​ነ​ጹት ሁሉ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ያር​ዱ​ላ​ቸው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በጉባኤውም ያልተቀደሱ እጅግ ሰዎች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ይቀድሱአቸው ዘንድ ንጹሐን ላልሆኑት ሁሉ ፋሲካውን ያርዱላቸው ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 30:17
6 交叉引用  

ይህን ሁሉ እንስሳ ዐርደው ቆዳውን ለመግፈፍ በቂ ካህናት ስላልነበሩ ሥራው እስኪጠናቀቅና የነጹ ካህናት እስከሚገኙ ድረስ ሌዋውያን ይረዱአቸው ነበር፤ በመንጻት ረገድ ከካህናት ይልቅ ሌዋውያን ዘወትር ዝግጁዎች ነበሩ።


እነዚህንም እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ጠብቁአቸው። በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ የእስራኤል ኅብረተሰብ ሁሉ እንስሶቹን ይረዱ።


እነርሱ በቤተ መቅደሱ በር ጠባቂነት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሰዎች የሚያቀርቡአቸውን መሥዋዕቶች በማረድ፥ እንዲሁም ሰዎችን በማገልገል እንዲሠሩ ይፈቅድላቸዋል።


“እኛ በድን በመንካታችን ረክሰናል፤ ነገር ግን ከቀሩት እስራኤላውያን ተለይተን በወቅቱ ለእግዚአብሔር መባ እንዳናቀርብ ስለምን እንከለከላለን?”


የአይሁድ የፋሲካ በዓል ቀርቦ ነበር፤ ብዙዎቹም የፋሲካ በዓል ከመድረሱ በፊት፥ ራሳቸውን ለማንጻት ከየቦታው ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤


跟着我们:

广告


广告