Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 30:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የበግ ጠቦቶችን ለፋሲካ በዓል መሥዋዕት አድርገው ዐረዱ፤ በዚህ ጊዜ ራሳቸውን ያላነጹ ካህናትና ሌዋውያን በጣም አፈሩ፤ ከዚህም የተነሣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለዩ፤ ከዚያም በኋላ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ቻሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በሁለተኛው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን በግ ዐረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ ዐፍረው ስለ ነበር ራሳቸውን ቀደሱ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አመጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በሁለተኛውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን ጠቦት አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አዋረዱ፥ ተቀደሱም፥ ወደ ጌታም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ አረዱ፤ ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ተዘ​ጋጁ ነጹም። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አመጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በሁለተኛውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም አፈሩ፤ ተቀደሱም፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 30:15
16 交叉引用  

እነዚህም ሰዎች ሌዋውያን ወገኖቻቸውን ሰብስበው ሁሉም በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት ራሳቸውን አነጹ፤ ከዚህም በኋላ ንጉሡ እንዳዘዛቸው ሌዋውያኑ በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት ቤተ መቅደሱን አነጹ፤


በዚህ ዐይነት ሕዝቡ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ያመጡአቸው እንስሶች ብዛት ሰባ ኰርማዎች፥ አንድ መቶ የበግ አውራዎችና ሁለት መቶ የበግ ጠቦቶች ነበሩ።


ይህን ሁሉ እንስሳ ዐርደው ቆዳውን ለመግፈፍ በቂ ካህናት ስላልነበሩ ሥራው እስኪጠናቀቅና የነጹ ካህናት እስከሚገኙ ድረስ ሌዋውያን ይረዱአቸው ነበር፤ በመንጻት ረገድ ከካህናት ይልቅ ሌዋውያን ዘወትር ዝግጁዎች ነበሩ።


በሁለተኛው ወር የቂጣን በዓል ለማክበር ብዙ ሰዎች በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።


ንጉሥ ሕዝቅያስ አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ ሰባት ሺህ በጎችንና ፍየሎችን፥ ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች ደግሞ አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ ዐሥር ሺህ በጎችንና ፍየሎችን ዐርደው እንዲበሉ ለሕዝቡ ሰጡ፤ ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ካህናትም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለዩ፤


እነዚህ ካህናትና ሌዋውያን ራሳቸውን የቀደሱ ታማኞች ስለ ነበሩ የሚመዘገቡት ከሚስቶቻቸው ከልጆቻቸውና በእነርሱ ሥር ከሚተዳደሩት ሰዎች ሁሉ ጋር በአንድነት ነበር፤


ወገኖቻችሁ የሆኑ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ ይከተሉ ዘንድ ራሳችሁን አንጽታችሁ የፋሲካን በግ ዕረዱ።”


እዚያ የነበሩት ካህናት ሁሉ የአገልግሎት ምድባቸውን ሳይመለከቱ በአንድነት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሰጥተው ነበር፤


ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ በሥርዓቱ መሠረት ራሳቸውን አነጹ፤ ሌዋውያኑም በፋሲካው በዓል አከባበር ላይ ከምርኮ ለተመለሱት ሕዝብና ለካህናቱ፥ እንዲሁም ለራሳቸው የቀረቡትን እንስሶች ዐረዱ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፥ “ወደ ሰዎቹ ሂድ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ አድርገህ ታቀርባቸው ዘንድ ዛሬና ነገ ሰውነታቸውን እንዲያነጹና ልብሳቸውንም እንዲያጥቡ ንገራቸው፤


ለአገልግሎት ወደ እኔ የሚቀርቡ ካህናት እንኳ ሳይቀሩ ራሳቸውን ያንጹ፤ ይህ ካልሆነ እኔ እግዚአብሔር እቀጣቸዋለሁ።”


ዘግይተው ሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት እንዲያከብሩ ተፈቅዶላቸዋል፤ ሲያከብሩም እርሾ የሌለበትን ቂጣ ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉ።


跟着我们:

广告


广告