2 ዜና መዋዕል 30:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1-3 ራሳቸውን ያነጹ በቂ ካህናት ስላልነበሩና በኢየሩሳሌም ብዙ ሕዝብ ስላልተሰበሰበ፥ ሕዝቡ የፋሲካን በዓል እንደ ተለመደው በመጀመሪያው ወር ሊያከብር አልቻለም፤ ስለዚህ ንጉሥ ሕዝቅያስ፥ ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖችና የኢየሩሳሌም ሕዝብ የፋሲካ በዓል በሁለተኛው ወር እንዲከበር ተስማምተው ወሰኑ፤ በዚህ መሠረት ንጉሡ ለመላው የእስራኤልና የይሁዳ እንዲሁም የኤፍሬምና የምናሴ ሕዝብ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር በፋሲካ በዓል ተካፋዮች ይሆኑ ዘንድ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መቅደስ እንዲመጡ የጥሪ ደብዳቤ ላከላቸው፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ሕዝቅያስ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማክበር በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዲመጡ፣ ለመላው እስራኤልና ለይሁዳ መልእክት ላከ፤ ለኤፍሬምና ለምናሴም ደብዳቤ ጻፈ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ለእስራኤልም አምላክ ለጌታ ፋሲካን ለማክበር ወደ ጌታ ቤት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ሕዝቅያስ ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፥ ደግሞም ወደ ኤፍሬምና ወደ ምናሴ ደብዳቤ ጻፈ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ፋሲካ ያደርጉ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ሕዝቅያስ ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤ ደግሞም ወደ ኤፍሬምና ወደ ምናሴ ደብዳቤዎችን ጻፈ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ፋሲካ ያደርጉ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ሕዝቅያስ ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤ ደግሞም ወደ ኤፍሬምና ወደ ምናሴ ደብዳቤ ጻፈ። 参见章节 |