2 ዜና መዋዕል 29:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ይህን ሁሉ በተፋጠነ አኳኋን ለማከናወን እግዚአብሔር ስለ ረዳቸው እጅግ ተደሰቱ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም36 ሕዝቅያስና ሕዝቡ፣ ነገሩ ሁሉ እንዲህ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲከናወን እግዚአብሔር ስለ ረዳቸው ሐሤት አደረጉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 ሕዝቅያስና ሕዝቡም ሁሉ ጌታ ለሕዝቡ ስላዘጋጀላቸው ነገር ደስ አላቸው። ይህም ነገር በድንገት ተደረገ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 ሕዝቅያስና ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ስላዘጋጀው ነገር ደስ አላቸው። ይህ ነገር በድንገት ተደርጎአልና። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 ሕዝቅያስና ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ስላዘጋጀላቸው ነገር ደስ አላቸው። ይህም ነገር በድንገት ተደረገ። 参见章节 |
ራሳቸውን ያነጹ በቂ ካህናት ስላልነበሩና በኢየሩሳሌም ብዙ ሕዝብ ስላልተሰበሰበ፥ ሕዝቡ የፋሲካን በዓል እንደ ተለመደው በመጀመሪያው ወር ሊያከብር አልቻለም፤ ስለዚህ ንጉሥ ሕዝቅያስ፥ ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖችና የኢየሩሳሌም ሕዝብ የፋሲካ በዓል በሁለተኛው ወር እንዲከበር ተስማምተው ወሰኑ፤ በዚህ መሠረት ንጉሡ ለመላው የእስራኤልና የይሁዳ እንዲሁም የኤፍሬምና የምናሴ ሕዝብ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር በፋሲካ በዓል ተካፋዮች ይሆኑ ዘንድ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መቅደስ እንዲመጡ የጥሪ ደብዳቤ ላከላቸው፤