Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 መሥዋዕቱን የማቅረብ ሥራ በተፈጸመ ጊዜ ንጉሥ ሕዝቅያስና በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 መሥዋዕቱ ሁሉ ቀርቦ ካበቃ በኋላ፣ ንጉሡና ዐብረውት የነበሩት ሁሉ ተንበርክከው ሰገዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ማቅረቡንም በፈጸሙ ጊዜ ንጉሡና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሁሉ አጐነበሱ ሰገዱም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ማቅ​ረ​ቡ​ንም በፈ​ጸሙ ጊዜ ንጉሡ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሁሉ አጐ​ነ​በሱ፤ ሰገ​ዱም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ማቅረቡንም በፈጸሙ ጊዜ ንጉሡና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሁሉ አጎነበሱ፤ ሰገዱም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:29
10 交叉引用  

የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፤


ከዚህ በኋላ ዳዊት ሕዝቡን “አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ!” አለ፤ መላው ጉባኤም የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ወደ መሬት ለጥ ብለውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ለንጉሡም ክብር ሰጡ።


ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮሣፍጥና ከእርሱ ጋር የነበሩት የይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤


በዚያ የነበረ ሕዝብም ሁሉ በኅብረት ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መሥዋዕቱም ሁሉ ፈጽሞ እስከሚቃጠል ድረስ እምቢልተኞቹ እምቢልታቸውን ይነፉ ነበር።


እስራኤላውያን እሳት ከሰማይ ሲወርድና የእግዚአብሔርም ክብር በቤተ መቅደስ ላይ ማረፉን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው፦ “እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነው!” እያሉ ሰገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።


ነገሥታት ሁሉ ይስገዱለት፤ ሕዝቦች ሁሉ ያገልግሉት።


ኑ፤ ዝቅ ብለን እንስገድ! በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ!


ግርማ በተመላ ቅድስናው ለእግዚአብሔር ስገዱ! የምድር ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጡ!


ምክንያቱም፦ “እኔ ሕያው ነኝ ይላል እግዚአብሔር፤ ሰው ሁሉ በጒልበቱ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤ በአንደበቱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይመሰክራል” ተብሎ ተጽፎአል።


跟着我们:

广告


广告