Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ካህናቱም በመጀመሪያ ኰርማዎቹን፥ ቀጥሎም በጎቹን፥ በመጨረሻም የበግ ጠቦቶቹን ዐርደው የእያንዳንዱን መሥዋዕት ደም በመሠዊያው ላይ ረጩት፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ካህናቱም ወይፈኖቹን ዐርደው ደሙን በመውሰድ በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ አውራ በጎቹንም ዐርደው ደሙን በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ እንደዚሁም ጠቦቶቹን ዐርደው ደሙን በመሠዊያው ላይ ረጩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ወይፈኖቹንም አረዱ፥ ካህናቱም ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ አውራ በጎቹንም አረዱ፥ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ ጠቦቶቹንም አረዱ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ወይ​ፈ​ኖ​ቹ​ንም አረዱ፤ ካህ​ና​ቱም ደሙን ተቀ​ብ​ለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጩት፤ አውራ በጎ​ቹ​ንም አረዱ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጩት፤ ጠቦ​ቶ​ቹ​ንም አረዱ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ወይፈኖቹንም አረዱ፤ ካህናቱም ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ላይ ረጩት። አውራ በጎቹንም አረዱ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ ጠቦቶቹንም አረዱ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:22
9 交叉引用  

ለፋሲካውም በዓል የታረዱትን የበግና የፍየል ጠቦቶች ሌዋውያኑ ቆዳቸውን ገፈፉአቸው፤ ካህናቱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ረጩ፤


ያ ሰው ወይፈኑን በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ትውልዳቸው ከአሮን ወገን የሆነ ካህናት ደሙን ወደ እግዚአብሔር ያቅርቡት፤ በድንኳኑ በር መግቢያ በኩል በሚገኘው መሠዊያ ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።


ደግሞም ጥቂት ደም ወስዶ በድንኳኑ በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ባለው በመሠዊያው ጒጦች ላይ ያኑር፤ ከዚያም የተረፈውን ደም በድንኳኑ መግቢያ በኩል የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፍስሰው።


ካህኑም የእንስሳይቱን ደም በጣቱ እያጠቀሰ በሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያው አራት ማእዘን በሚገኙ ጒጦች ላይ ያኑር፤ ከዚህም የተረፈውን ደም በመሠዊያው ሥር ያፍስሰው፤


ከዚያም ደግሞ ጥቂት ደም ወስዶ በድንኳኑ ውስጥ በዕጣን መሠዊያው አራት ማእዘን ጒጦች ላይ ያኑር፤ የተረፈውን ደም ግን በድንኳኑ መግቢያ በኩል የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፍስሰው።


ሙሴም ዐረደው፤ ደሙንም በመሠዊያው አራት ማእዘን ረጨ፤


ቀጥሎም የአሮንን ልጆች ወደ ፊት አቅርቦ የቀኝ ጆሮዎቻቸውን ጫፎች፥ የቀኝ እጆቻቸውን አውራ ጣቶችና የቀኝ እግሮቻቸውን አውራ ጣቶች ቀባ፤ ከዚህ የተረፈውንም ደም ሙሴ በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ረጨው።


跟着我们:

广告


广告