Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እነርሱም ለንጉሣዊው ቤተሰብና ለይሁዳ ሕዝብ የኃጢአት ስርየት፥ እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ መንጻት መሥዋዕት ሆነው ለእግዚአብሔር ይቀርቡ ዘንድ ሰባት ኰርማዎችን፥ ሰባት የበግ አውራዎችን፥ ሰባት የበግ ጠቦቶችንና ሰባት ፍየሎችን አመጡ፤ ንጉሡም የአሮን ዘሮች የሆኑትን ካህናት እንስሶቹን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ አዘዛቸው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እነርሱም ስለ መንግሥቱ፣ ስለ መቅደሱና ስለ ይሁዳ ሰባት ወይፈኖች፣ ሰባት አውራ በጎች፣ ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና ሰባት ተባዕት የፍየል ጠቦቶች ለኀጢአት መሥዋዕት አቀረቧቸው፤ ንጉሡም እነዚህን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ እንዲያቀርቡ የአሮንን ዘሮች ካህናቱን አዘዘ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ስለ መንግሥቱና ስለ መቅደሱም ስለ ይሁዳም ሰባት ወይፈኖች፥ ሰባትም አውራ በጎች፥ ሰባትም የበግ ጠቦቶች፥ ሰባትም አውራ ፍየሎች ለኃጢአት መሥዋዕት አመጡ። የአሮንንም ልጆች ካህናቱን፦ “በጌታ መሠዊያ ላይ አሳርጉአቸው” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ስለ መን​ግ​ሥ​ቱና ስለ መቅ​ደ​ሱም፥ ስለ ሕዝ​ቡም ስለ እስ​ራ​ኤል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሰባት ወይ​ፈ​ኖች፥ ሰባ​ትም አውራ በጎች፥ ሰባ​ትም የበግ ጠቦ​ቶች፥ ሰባ​ትም አውራ ፍየ​ሎች አመጡ። የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች ካህ​ና​ቱን፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ውጡ” አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ስለ መንግሥቱና ስለ መቅደሱም ስለ ይሁዳም ሰባት ወይፈኖች፥ ሰባትም አውራ በጎች፥ ሰባትም የበግ ጠቦቶች፥ ሰባትም አውራ ፍየሎች ለኃጢያት መሥዋዕት አመጡ። የአሮንንም ልጆች ካህናቱን “በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አሳርጉአቸው” አላቸው።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:21
12 交叉引用  

የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያን እግዚአብሔር ስለ ረዳቸው ሰባት ኰርማዎችንና ሰባት በጎችን ሠዉ፤


በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ የከተማይቱን ባለሥልጣኖች ሰብስቦ እነርሱን በማስከተል ወደ ቤተ መቅደሱ ሄደ፤


ከዚያም ቀጥሎ እነዚያ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን መባ ሁሉ አመጡ፤ በዚህ ዐይነት በመላው እስራኤል ሕዝብ ስም ዐሥራ ሁለት ኰርማዎችን፥ ዘጠና ስድስት የበግ አውራዎችንና ሰባ ሰባት የበግ ጠቦቶችን አቀረቡ፤ እንዲሁም ስለ ኃጢአታቸው ስርየት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎችን አቀረቡ፤ እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ።


ስለዚህ አሁን ሰባት ኰርማዎችንና ሰባት አውራ በጎችን ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ እዚያም ስለ ራሳችሁ ኃጢአት የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን ሰምቼ በበደላችሁ መጠን አልቀጣችሁም፤ እናንተ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ትክክል የሆነውን ነገር አልተናገራችሁም።”


በዓሉ በሚከበርባቸው ሰባት ዕለቶች በእያንዳንዱ ቀን ምንም ነውር የሌለባቸውን ሰባት ኰርማዎችና ሰባት የበግ አውራዎች በሙሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን ያዘጋጃል፤ ከዚህም ጋር በእያንዳንዱ ዕለት ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን አንድ የፍየል አውራ ያዘጋጃል።


“የእስራኤልም ማኅበር ስለ ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት ሁለት ተባዕት ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ለአሮን ያምጡለት።


በለዓምም ባላቅን “በዚህ ቦታ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፤ እንዲሁም ሰባት ኰርማዎችና ሰባት አውራ በጎች አምጣልኝ” አለው።


ከዚያም በፒስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው ወደ ጾፊም መስክ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ።


በለዓምም “በዚህ ቦታም ሰባት መሠዊያዎችን ሥራልኝ፤ ሰባት ኰርማዎችና ሰባት የበግ አውራዎችም አምጣልኝ” አለው።


እኛ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተካፋዮች እንድንሆን እግዚአብሔር ኃጢአት የሌለበትን ክርስቶስን የእኛን ኃጢአት እንዲሸከም አደረገው።


跟着我们:

广告


广告