Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እንዲሁም ንጉሥ አካዝ ለእግዚአብሔር ታማኝ ባልነበረባቸው ዓመቶች ወስዶት የነበረውን ዕቃ ሁሉ መልሰን በማምጣት ለእግዚአብሔር የተለዩ እንዲሆኑ አድርገናል፤ እነዚህም ዕቃዎች በሙሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ፊት ለፊት ባለው ስፍራ ይገኛሉ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ንጉሥ አካዝ ነግሦ ሳለ ባለመታመኑ ከቦታቸው ያነሣቸውን ዕቃዎች ሁሉ አዘጋጅተን ቀድሰናቸዋል፤ እነሆ፤ ዕቃዎቹ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠዊያ ፊት ለፊት ናቸው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ንጉሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመተላለፍ ያረከሰውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅተናል ቀድሰናልም፤ እነሆም፥ በጌታ መሠዊያ ፊት ተቀምጠዋል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ንጉ​ሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመ​ተ​ላ​ለፉ ያረ​ከ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል፤ ቀድ​ሰ​ና​ልም፤ እነ​ሆም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ሆነ​ዋል” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ንጉሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመተላለፍ ያረከሰውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅተናል ቀድሰናልም፤ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ሆነዋል” አሉት።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:19
5 交叉引用  

ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያና በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ አካዝም ያንን መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን በኩል አኖረው፤


ንጉሥ አካዝ በቤተ መቅደስ ውስጥ መገልገያ የነበሩትን ከነሐስ የተሠሩ መንኰራኲሮች ቈርጦ ልሙጥ የሆነውን ነገር ከጐናቸው ወሰደ። በእነርሱ ላይ የነበሩትንም የመታጠቢያ ሳሕኖች ወሰደ፤ ከነሐስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ከታች በኩል ተሸክመውት ከነበሩት ከነሐስ ከተሠሩት ከዐሥራ ሁለት የበሬ ቅርጾች ጀርባ ላይ አንሥቶ፥ ከድንጋይ በተሠራ መሠረት ላይ አኖረው።


በተጨማሪም አካዝ የቤተ መቅደሱን ዕቃ ሁሉ አውጥቶ ሰባበረው፤ ቤተ መቅደሱንም ዘጋ፤ በኢየሩሳሌምም በየስፍራው የጣዖት መሠዊያዎችን አቆመ፤


ሌዋውያኑ ስለ ተከናወነው ሥራ ለንጉሥ ሕዝቅያስ የሚከተለውን መግለጫ አቀረቡ፦ “የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ፥ የተቀደሰው ኅብስት የሚቀመጥበትን ገበታና ከእነርሱም ጋር የተያያዙትን ሌሎች ዕቃዎች ጭምር ቤተ መቅደሱን በሙሉ አንጽተናል፤


በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ የከተማይቱን ባለሥልጣኖች ሰብስቦ እነርሱን በማስከተል ወደ ቤተ መቅደሱ ሄደ፤


跟着我们:

广告


广告