Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የማንጻቱ ሥራ በመጀመሪያው ወር መባቻ ቀን ተጀምሮ በስምንተኛው ቀን ወደ ቤተ መቅደስ የሚያስገባው ክፍል ጭምር ሙሉ በሙሉ ተፈጸመ፤ ከዚህ በኋላም ቤተ መቅደሱን ለአምልኮ ሥነ ሥርዓት ለማዘጋጀት በተከታዮቹ ስምንት ቀኖች ማለትም ወሩ በገባ እስከ ዐሥራ ስድስተኛው ቀን ድረስ ሠሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ማንጻቱንም በመጀመሪያው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን ጀምረው በዚያ ወር በስምንተኛው ቀን እስከ መቅደስ ሰበሰብ ደረሱ፤ በሚቀጥሉትም ስምንት ቀናት የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቀደሱ፤ የመቀደሱም ሥራ በመጀመሪያው ወር በዐሥራ ስድስተኛው ቀን ተጠናቀቀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በመጀመሪያውም ወር በመጀመሪያው ቀን ይቀድሱ ጀመር፥ በዚያውም ወር በስምንተኛው ቀን ወደ ጌታ ቤት ዋና የመግቢያ ደጅ ደረሱ የጌታንም ቤት በስምንት ቀን ውስጥ ቀደሱት፥ በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ ስድስተኛው ቀን ፈጸሙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ያነጹ ጀመር፤ በዚ​ያ​ውም ወር በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወለል ደረሱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በስ​ም​ንት ቀን አነጹ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ስድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በመጀመሪያውም ወር በመጀመሪያው ቀን ይቀድሱ ጀመር፤ በዚያውም ወር በስምንተኛው ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ወለል ደረሱ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት በስምንት ቀን ቀደሱ፤ በመጀመሪያውም ወር በአሥራ ስድስተኛው ቀን ፈጸሙ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:17
8 交叉引用  

በመግቢያው በር የሚገኘው በረንዳ ቁመቱ አራት ሜትር ተኩል፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ዘጠኝ ሜትር ነበር።


ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞን የቤተ መቅደሱን የዕቃ ግምጃ ቤቶቹን፥ በደርቡና በምድር ቤቱ የሚገኙትን ክፍሎችና ኃጢአት የሚሰረይበትን የቅድስተ ቅዱሳኑን አሠራር የሚገልጥ ዕቅድ ሰጠው።


ሌዋውያኑ ስለ ተከናወነው ሥራ ለንጉሥ ሕዝቅያስ የሚከተለውን መግለጫ አቀረቡ፦ “የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ፥ የተቀደሰው ኅብስት የሚቀመጥበትን ገበታና ከእነርሱም ጋር የተያያዙትን ሌሎች ዕቃዎች ጭምር ቤተ መቅደሱን በሙሉ አንጽተናል፤


ሕዝቅያስ በነገሠበት ዓመት በመጀመሪያው ወር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በር ሁሉ እንደገና ከፍቶ አደሰ፤


የቤተ መቅደሱን በር ሁሉ ዘጉ፤ መብራቶቹንም አጠፉ፤ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ዕጣንን ማጠን ወይም የሚቃጠል መሥዋዕትን ማቅረብ ተዉ፤


በመግቢያው በር ያለው በረንዳም ቁመቱ ኀምሳ አራት ሜትር ሲሆን፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ወርድ ዘጠኝ ሜትር ነው፤ ውስጡም በንጹሕ ወርቅ እንዲለበጥ አደረገ።


跟着我们:

广告


广告