Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 28:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በዚሁ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን በምዕራባዊ ኰረብቶች ግርጌና በደቡባዊ ይሁዳ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞች ወረሩ፤ ቤትሼሜሽ፥ አያሎን፥ ገዴሮት፥ ሶኮ፥ ቲምናና ጊምዞ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች በድል አድራጊነት ያዙ፤ በዚያም ኖሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በየኰረብታው ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ያሉትን ከተሞች በመውረር ቤትሳሚስን፣ ኤሎንን፣ ግዴሮትን፣ ሦኮን፣ ተምናን፣ ጊምዞንና በአካባቢያቸው የሚገኙትን መንደሮች ሁሉ ያዙ፤ ተቀመጡባቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ደግሞም ፍልስጤማውያን በቈላውና በደቡብ በኩል ባሉት በይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤትሳሚስንና ኤሎንን፥ ግዴሮትንም፥ ሦኮንና መንደሮችዋን፥ ተምናንና መንደሮችዋን፥ ጊምዞንና መንደሮችዋን ወስደው በዚያ ተቀምጠው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ደግ​ሞም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቆ​ላ​ውና በደ​ቡብ በኩል ባሉት በይ​ሁዳ ከተ​ሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤት​ሳ​ሚ​ስ​ንና ኤሎ​ንን፥ ጋቤ​ሮ​ት​ንም፥ ሠካ​ዕ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ቴም​ና​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም፥ ጋማ​ዚ​እ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወስ​ደው በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ደግሞም ፍልስጤማውያን በቈላውና በደቡብ በኩል ባሉት በይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤትሳሚስንና ኤሎንን፥ ግዴሮትንም፥ ሦኮንና መንደሮችዋን፥ ተምናንና መንደሮችዋን፥ ጊምዞንና መንደሮችዋን ወስደው በዚያ ተቀምጠው ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 28:18
13 交叉引用  

ፍልስጥኤማውያንንም ድል ነሥቶ ከትንሽ መንደር እስከ ታላቅ ከተማ ጋዛንና በዙሪያው የሚገኘውን ግዛት ጭምር እነርሱ የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ ወረረ።


ጾርዓ፥ አያሎንና ኬብሮን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።


ቤትጹር፥ ሶኮ፥ ዐዱላም፥


እርሱ ከምሥራቅ ሶርያውያንን፥ ከምዕራብ ፍልስጥኤማውያንን ልኮ እስራኤልን እንዲወሩ አደረገ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ቊጣው አልበረደም፤ ስለዚህ እጁ እነርሱን ለመቅጣት እንደ ተቃጣ ነው።


“አሁን ግን አንቺን ለመቅጣትና ድርሻሽ የሆነውንም በረከት ከአንቺ ለመቀነስ እጄን ዘርግቼአለሁ፤ እነርሱ የፈለጉትን እንዲያደርጉ አንቺን ለጠላቶችሽ፥ ብልግናሽ ለሚያስደነግጣቸው ለፍልስጥኤማውያን አሳልፌ ሰጥቼሻለሁ።


ይህንንስ ያደረግሽው የአንቺ በደል ከመታወቁ በፊት አይደለምን? አሁን ግን አንቺ ለሶርያ ከተሞችና ለጐረቤቶቻቸው እንዲሁም ለፍልስጥኤም ከተሞችና ባካባቢው ላሉ ለሚንቁሽ ሁሉ መሳለቂያ ሆነሻል።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ፍልስጥኤማውያን በማያቋርጥ ጠላትነት በቀልን ተበቅለዋል፤ ይህም የጥፋት በቀል ተንኰልን በተመላ ልብ ነበር።


ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል።


ገዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማና ማቄዳ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል።


በኮረብታማውም አገር ሻሚር፥ ያቲር፥ ሶኮህ፥


አንድ ቀን ሶምሶን ወደ ቲምና ወረደ፤ በዚያም አንዲት ፍልስጥኤማዊት ሴት አየ፤


ፍልስጥኤማውያን ሶኮ ተብላ በምትጠራው በይሁዳ ለጦርነት ተሰለፉ፤ እነርሱም በሶኮና በዐዜቃ መካከል ኤፌስዳሚም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሰፍረው ነበር።


ከዚህም በኋላ አካሄዱን ተመልከቱት፤ አቅጣጫው ወደ ቤትሼሜሽ ከተማ ያመራ እንደ ሆነ ይህን አሠቃቂ መቅሠፍት በእኛ ላይ የላከብን እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፤ ወደዚያ አቅጣጫ ባያመራ ግን መቅሠፍቱ የመጣብን በአጋጣሚ እንጂ እግዚአብሔር የላከብን አለመሆኑን እንገነዘባለን።”


跟着我们:

广告


广告