Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 26:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ዖዝያ ለጦርነት ዝግጁ የሆነ እጅግ የበዛ ሠራዊት ነበረው፤ የሠራዊቱም አባላት ስም ዝርዝር የንጉሡ ጸሐፊዎች በሆኑት በይዒኤልና በማዕሤያ ይመዘገብ ነበር፤ የእነርሱም የበላይ ተቈጣጣሪ የቤተ መንግሥቱ ሠራተኞች አባል የሆነው ሐናንያ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ዖዝያን ከንጉሡ ሹማምት አንዱ በሆነው በሐናንያ መሪነት፣ በጸሓፊው በይዒኤልና በአለቃው በመዕሤያ አማካይነት ተሰብስቦ በተቈጠረው መሠረት በየምድቡ ለጦርነት ዝግጁ ሆኖ የሚወጣ፣ በሚገባ የሠለጠነ ሰራዊት ነበረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ደግሞም ለዖዝያን በሠራዊቱ ውስጥ ለውግያ ብቁ የሆኑ ወታደሮች ነበሩት፤ በንጉሡ አለቃ በሐናንያ ትእዛዝ በአለቃው በመዕሤያና በጸሐፊው በይዒኤል እጅ እንደ ተቈጠሩ ወደ ሰልፍ በየቁጥራቸው ይወጡ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ደግ​ሞም ለዖ​ዝ​ያን የሰ​ልፍ ሠራ​ዊት ነበ​ሩት፤ በን​ጉሡ አለቃ በሐ​ና​ንያ ትእ​ዛዝ፥ በአ​ለ​ቃው በመ​ዕ​ሤ​ያና በጸ​ሓ​ፊው በኢ​ዮ​ሔል እጅ እንደ ተቈ​ጠሩ ወደ ሰልፍ በየ​ቍ​ጥ​ራ​ቸው ይወጡ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ደግሞም ለዖዝያን በሠራዊት ውስጥ ሰልፈኞች ነበሩት፤ በንጉሡ አለቃ በሐናንያ ትእዛዝ በአለቃው በመዕሤያና በጸሐፊው በይዒኤል እጅ እንደ ተቋጠሩ ወደ ሰልፍ በየቍጥራቸው ይወጡ ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 26:11
3 交叉引用  

ሶርያውያን በእስራኤላውያን ላይ ወረራ በፈጸሙበት በአንድ ወቅት፥ አንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጃገረድ ማርከው ወስደው ነበር፤ እርስዋም ለንዕማን ሚስት፥ ገረድ ሆና ትኖር ነበር።


በምዕራባዊ ኰረብቶች ግርጌና በሜዳዎች ላይ ብዙ የቀንድ ከብቶች ስለ ነበሩትም በገጠር የተመሸጉ መጠበቂያ ግንቦችን ሠራ፤ ብዙ ጒድጓዶችንም ማሰ፤ ግብርና ይወድ ስለ ነበረ በኰረብታማ አገሮችና በለሙ ቦታ የወይን ተክል ተካዮችና ገበሬዎች ነበሩት።


ሠራዊቱም የሚመራው በሁለት ሺህ ስድስት መቶ የጐሣ መሪዎች ነበር፤


跟着我们:

广告


广告