Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 25:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ልጆቻቸውንም ያልገደለበት ምክንያት እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ሕግ “ወላጆች ልጆቻቸው በፈጸሙት ወንጀል፥ ልጆችም ወላጆቻቸው በፈጸሙት ወንጀል በሞት አይቀጡም፤ አንድ ሰው በሞት መቀጣት ያለበት ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ ነው” ሲል የተናገረውን ቃል በማክበር ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር በሙሴ መጽሐፍ በተጻፈው ሕግ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢአቱ ይሙት እንጂ ወላጆች በልጆቻቸው አይገደሉ፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ኀጢአት አይገደሉ” ብሎ ባዘዘው መሠረት አደረገ እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አሜስያስ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደለም ነበር ምክንያቱም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈ፥ ጌታ እንዲህ ብሎ አዝዞ ነበርና፦ “ሰው ሁሉ በገዛ ኃጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆች ፋንታ አይሙቱ፥ ልጆችም በአባቶች ፋንታ አይሙቱ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ቃል ኪዳን እንደ ተጻፈ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢ​አቱ ይሙት እንጂ አባ​ቶች በል​ጆ​ቻ​ቸው፥ ልጆ​ችም በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ፋንታ አይ​ሙቱ” ብሎ እን​ዳ​ዘዘ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ግን አል​ገ​ደ​ለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም “ሰው ሁሉ በገዛ ኃጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆች ፋንታ አይሙቱ፤ ልጆችም በአባቶች ፋንታ አይሙቱ” ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮችን ልጆች አልገደለም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 25:4
6 交叉引用  

ንጉሥ አሜስያስ የይሁዳና የብንያም ነገዶች የሆኑትን ወንዶች ሁሉ በየጐሣዎቻቸው በቡድን በቡድን በመደልደል በየቡድኑ በሺህ አለቆችና በመቶ አለቆች ሥር መደበ፤ በቡድን የተመደቡትም ሰዎች ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶችን ሁሉ የሚያጠቃልል ሲሆን ብዛታቸውም ሦስት መቶ ሺህ ነበር፤ እነርሱም ለጦርነት የተዘጋጁ፥ በጦርና በጋሻ አያያዝ የሠለጠኑ ምርጥ ወታደሮች ነበሩ፤


ሞት የሚገባው ኃጢአት ለሚሠራ ሰው ብቻ ነው፤ ልጅ ስለ አባቱ ኃጢአት አይቀጣም፤ አባትም ስለ ልጁ ኃጢአት አይቀጣም፤ ደግ ሰው በደግነቱ መልካም ዋጋውን ያገኛል፤ ክፉ ሰውም በክፋቱ ይቀጣል።


የእያንዳንዱ ሰው ሕይወት የእኔ ነው፤ የወላጅም ሆነ የልጅ ሕይወት የእኔ መሆኑን ዕወቁ፤ ኃጢአት የሚሠራ ሰው ራሱ ይሞታል።


“ልጆቻቸው በሠሩት ወንጀል ወላጆች በሞት መቀጣት የለባቸውም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ወንጀል ልጆቻቸው በሞት አይቀጡ፤ እያንዳንዱ ሰው በሠራው ወንጀል በሞት ይቀጣ።


跟着我们:

广告


广告