2 ዜና መዋዕል 25:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ከዚህ በኋላ ንጉሥ አሜስያስና አማካሪዎቹ በእስራኤል ላይ አሤሩ፤ አሜስያስም የኢዩ የልጅ ልጅ የኢዮአካዝ ልጅ ወደ ሆነው ወደ እስራኤል ንጉሥ ዮአስ መልእክተኞች በመላክ “እንግዲህ፥ ና ይዋጣልን?” ሲል ለጦርነት አነሣሣው፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ አማካሪዎቹን ካማከረ በኋላ፣ የእስራኤል ንጉሥ የኢዩ የልጅ ልጅ፣ የኢዮአካዝ ልጅ ወደ ሆነው ወደ ኢዮአስ፣ “ናና ፊት ለፊት እንጋጠም” ሲል ላከበት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 የይሁዳም ንጉሥ አሜስያስ ተማክሮ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ኢዮአስ እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ና፥ እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 የይሁዳም ንጉሥ አሜስያስ ምክር አደረገና፥ “ና፥ እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ኢዮአስ ላከ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 የይሁዳም ንጉሥ አሜስያስ ምክር አደረገና “ና፥ እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ኢዮአስ ላከ። 参见章节 |