Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 21:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ነገር ግን የእስራኤልን ነገሥታት መጥፎ ምሳሌነት ተከተልክ፤ ልክ አክዓብና በእርሱ እግር የተተኩት ነገሥታት የእስራኤልን ሕዝብ በእግዚአብሔር እንዳይታመኑ እንዳደረጉት ሁሉ አንተም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለእግዚአብሔር ታማኞች እንዳይሆኑ አደረግህ፤ ከአንተ የተሻሉትን የአባትህን ቤት ወንድሞችህን እንኳ ሳይቀር ገደልካቸው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ነገር ግን በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደሃል፤ የአክዓብ ቤት የእስራኤልን ሕዝብ እንዲያመነዝር እንዳደረገ ሁሉ፣ አንተም ይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲያመነዝሩ አሳሳትሃቸው፤ እንዲሁም ካንተ የሚሻሉትን፣ የገዛ ወንድሞችህንና የአባትህን ቤተ ሰብ አባላት ገደልሃቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ግን ሄደሃልና፥ የአክዓብም ቤት እንዳደረገ ይሁዳንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እንዲያመነዝሩ አድርገሃልና፥ ከአንተም የሚሻሉትን የአባትህን ቤት ወንድሞችህን ገድለሃልና፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ግን ሄደ​ሃ​ልና፥ የአ​ክ​ዓ​ብም ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ ይሁ​ዳ​ንና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን እን​ዲ​ያ​መ​ነ​ዝሩ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ከአ​ን​ተም የሚ​ሻ​ሉ​ትን የአ​ባ​ት​ህን ቤት ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ገድ​ለ​ሃ​ልና፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ግን ሄደሃልና፥ የአክዓብም ቤት እንዳደረገ ይሁዳንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እንዲያመነዝሩ አድርገሃልና፥ ከአንተም የሚሻሉትን የአባትህን ቤት ወንድሞችህን ገድለሃልና፥ እነሆ፥

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 21:13
18 交叉引用  

ዖምሪ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ነገሥታት ይበልጥ የከፋ ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ።


ኢዮራምም “ኢዩ ሆይ፥ አመጣጥህ በሰላም ነውን?” ሲል ጠየቀ። ኢዩም፦ “እናትህ ኤልዛቤል ባመጣችው አስማትና የጣዖት አምልኮ ውስጥ ተነክረን እስካለን ድረስ ምን ሰላም አለ?” ሲል መለሰለት።


እርሱ በይሁዳ ኰረብቶች ላይ ሳይቀር እንኳ የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠራ፤ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራት እግዚአብሔርን እንዲያሳዝኑ አደረገ።


ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝብህን፥ ልጆችህንና ሚስቶችህን በብርቱ ይቀጣል፤ ንብረትህንም ሁሉ ያጠፋል፤


ኢዮራም መንግሥቱን ካጠናከረ በኋላ ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም አንዳንድ የእስራኤል ባለሥልጣኖችን ገደለ።


ከአክዓብ ሴቶች ልጆች አንዲቱን በማግባቱ፥ የንጉሥ አክዓብንና የሌሎቹን የእስራኤል ነገሥታት መጥፎ ምሳሌነት ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአትን ሠራ፤


ስለዚህ ሰዎቹም በቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ መስገድ ትተው፥ አሼራ ተብላ ለምትጠራ ሴት አምላክ ጣዖቶችና ምስሎች መስገድ ጀመሩ። ይህንንም ኃጢአት በመሥራታቸው የእግዚአብሔር ቊጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ።


ለከንቱ አማልክታቸው ሲሰግዱና መሥዋዕት ሲሠዉላቸው እንድትተባበሩአቸው ስለሚጠይቁአችሁ፥ እናንተም እነርሱ ለአማልክታቸው የሚያቀርቡትን ምግብ ለመብላት ስለምትፈተኑ፤ በአገሩ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ።


በምድር ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ስለ ኃጢአታቸው ለመቅጣት እግዚአብሔር ከሰማይ መኖሪያው ይገለጣል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ተሸሽገው የሚኖሩ የነፍሰ ገዳዮች ሥራ ይጋለጣል፤ ምድርም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ታጋልጣለች። የተገደሉትንም አትደብቅም።


ሰውን በመግደል ከተማን ለምትቈረቊሩና፥ በበደል ዋና ከተማን ለምትሠሩ ወዮላችሁ!


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተ በቅርብ ጊዜ እንደ ቀድሞ አባቶችህ ትሞታለህ፤ ከዚያ በኋላ ይህ ሕዝብ ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳል። እኔንም በመተው በሚወርሰው ምድር የሚገኙትን ጣዖቶች ያመልካል።


የሰይጣን ወገን እንደ ነበረውና ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየል መሆን አይገባንም፤ እርሱ ወንድሙን ስለምን ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ ስለ ነበረና የወንድሙ ሥራ ግን ትክክል ስለ ነበረ ነው።


跟着我们:

广告


广告