2 ዜና መዋዕል 20:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 ኢዮሣፍጥ የይሁዳ ንጉሥ የሆነው በሠላሳ አምስት ዓመቱ ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኻያ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱ ዐዙባ ተብላ የምትጠራ የሺልሒ ልጅ ነበረች፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም31 ኢዮሣፍጥ በይሁዳ ነገሠ። መንገሥ በጀመረ ጊዜም ዕድሜው ሠላሳ ዐምስት ዓመት ሲሆን፣ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ሃያ ዐምስት ዓመት ገዛ። እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 ኢዮሣፍጥም በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ መንገሥ በጀመረ ጊዜም የሠላሳ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሀያ አምስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 ኢዮሣፍጥም በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ መንገሥ በጀመረ ጊዜም የሠላሳ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ አምስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሳሊ ልጅ አዙባ ነበረች። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 ኢዮሣፍጥም በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ መንገሥ በጀመረ ጊዜም የሠላሳ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሀያ አምስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች። 参见章节 |