Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 20:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮሣፍጥና ከእርሱ ጋር የነበሩት የይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኢዮሣፍጥ በግንባሩ ወደ መሬት ተደፋ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ወደቁ፤ ሰገዱም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ኢዮሣፍጥም በግንባሩ ወደ ምድር ሰገደ ይሁዳም ሁሉ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ በጌታ ፊት በምድር በግንባራቸው ተደፍተው ለጌታ ሰገዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም በም​ድር ላይ ሰገደ፤ ይሁ​ዳም ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደቁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰገዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ኢዮሣፍጥም በምድር ላይ ተደፋ ይሁዳም ሁሉ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ በእግዚአብሔር ፊት ወደቁ፤ ለእግዚአብሔርም ሰገዱ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 20:18
8 交叉引用  

ሰውየውም በመንበርከክ ለእግዚአብሔር ሰግዶ፥


የቀዓትና የቆሬ ጐሣዎች አባላት የሆኑ ሌዋውያን ቆሙ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


መሥዋዕቱን የማቅረብ ሥራ በተፈጸመ ጊዜ ንጉሥ ሕዝቅያስና በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ።


እስራኤላውያን እሳት ከሰማይ ሲወርድና የእግዚአብሔርም ክብር በቤተ መቅደስ ላይ ማረፉን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው፦ “እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነው!” እያሉ ሰገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።


ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገነ። ሁሉም እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት “አሜን! አሜን!” ሲሉ መለሱ፤ ወደ ምድርም ለጥ ብለው ለእግዚአብሔር ሰገዱ።


ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢዮብ ተነሥቶ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ራሱን ተላጨ፤ በግምባሩም ወደ መሬት ተደፍቶ በመስገድ፥


ኑ፤ ዝቅ ብለን እንስገድ! በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ!


ሕዝቡም አመኑ፤ እግዚአብሔር ወደ እነርሱ መጥቶ እንደ ጐበኛቸውና የደረሰባቸውንም የግፍ ጭቈና ማየቱን በሰሙ ጊዜ ተንበርክከው ሰገዱ።


跟着我们:

广告


广告