Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 20:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሕዝቡ ጋር በነበረ በአንድ ሌዋዊ ላይ ወረደ፤ ይህም ሌዋዊ ያሐዚኤል ተብሎ የሚጠራ የዘካርያስ ልጅ ነበር፤ እርሱም በማታንያ፥ በይዒኤልና በበናያ በኩል ደግሞ የአሳፍ ወገን ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በዚህ ጊዜ የአሳፍ ዘር በሆነው በሌዋዊው በዘካርያስ ልጅ፣ በየሕዚኤል ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ መጣ። ዘካርያስም የበናያስ ልጅ ሲሆን፣ በናያስም የመታንያን ልጅ የሆነው የይዒኤል ልጅ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የጌታም መንፈስ ከአሳፍ ወገን በነበረው በሌዋዊው በማታንያ ልጅ በይዒኤል ልጅ በበናያስ ልጅ በዘካርያስ ልጅ በየሕዝኤል ላይ በጉባኤው መካከል መጣ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከአ​ሳፍ ወገን በነ​በ​ረው በሌ​ዋ​ዊው በም​ታ​ን​ያስ ልጅ በኢ​ያ​ሔል ልጅ በብ​ል​አ​ንያ ልጅ በዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ በኡ​ዝ​ሔል ላይ በጉ​ባ​ኤው መካ​ከል መጣ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእግዚአብሔርም መንፈስ ከአሳፍ ወገን በነበረው በሌዋዊው በማታንያ ልጅ፥ በይዒኤል ልጅ፥ በበናያስ ልጅ፥ በዘካርያስ ልጅ በየሕዝኤል ላይ በጉባኤው መካከል መጣ፤

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 20:14
11 交叉引用  

የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በዐዛርያስ ላይ ወረደ፤


የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በዚያው በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ቆመው ነበር፤


ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ ወረደ፤ እርሱም ሕዝቡ ሊያዩት በሚችሉበት ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ቆሞ “እግዚአብሔር ‘ትእዛዞቼን ስለምን ትተላለፋላችሁ? በገዛ ራሳችሁስ ላይ ስለምን ጥፋትን ታመጣላችሁ?’ ሲል ይጠይቃችኋል፤ እንግዲህ እናንተ ስለ ተዋችሁት እርሱም ትቶአችኋል” አላቸው።


ከዚያ በኋላ ትጸልያላችሁ፤ እኔም ጸሎታችሁን እሰማለሁ፤ የእርዳታ ጩኸት ትጮኻላችሁ፤ እኔም አለሁ እላችኋለሁ፤ እናንተ የጭቈናን ቀንበር ብታስወግዱ፥ የጣት ጥቆማንና የተንኰልን ንግግር ብታቆሙ፥


እኔን በልመና ከመጥራታቸው በፊት እመልስላቸዋለሁ፤ እየጸለዩም ሳለ እሰማቸዋለሁ።


የእስራኤል ሕዝብ በየነገዳቸው በቅደም ተከተል ተራ ሰፍረው አየ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ ስላደረበት፥


እንዲህም አለኝ፦ ‘ቆርኔሌዎስ ሆይ! እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቶአል፤ ለድኾች የምታደርገውም ምጽዋት ታስቦልሃል፤


ትኲር ብሎ ወደ መልአኩ ተመለከተና በመደንገጥ “ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?” አለ። መልአኩም እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህና ለድኾች የምታደርገው ምጽዋት መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጓል፤


跟着我们:

广告


广告