Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 19:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ፍትሕ ማጓደል ወይም ማድላት ወይም ጉቦ መቀበል በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ የሌሉ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን በመፍራት ትክክለኛ ፍርድ ስጡ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ማጣመም፣ አድልዎ ማድረግና መማለጃ መቀበል ስለሌለ ተጠንቅቃችሁ ፍረዱ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንግዲህ አሁን ጌታን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በጌታ ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉንም ነገር ተጠንቅቃችሁ አድርጉ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በእ​ና​ንተ ላይ ይሁን፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በደ​ልና ለሰው ፊት ማድ​ላት፥ መማ​ለ​ጃም መው​ሰድ የለ​ምና ሁሉን ተጠ​ን​ቅ​ቃ​ችሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉን ተጠንቅቃችሁ አድርጉ” አላቸው።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 19:7
27 交叉引用  

በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”


በሦስተኛው ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው ስለ ሆንኩ እንዲህ ብታደርጉ ሕይወታችሁን ታድናላችሁ፤


የእስራኤል አምላክ ይህን ተናግሮአል፤ የእስራኤል ጠባቂ እንዲህ ብሎኛል፤ “እግዚአብሔርን በመፍራትና በፍትሕ የሚያስተዳድር ንጉሥ፥


ከእኔ በፊት የሕዝብ ገዢ ሆኖ የተሾመው ሁሉ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመሆን፥ በየቀኑ ለምግብና ለመጠጥ የሚሆን አርባ ብር ያስከፍላቸው ነበር፤ የገዢዎቹም አገልጋዮች እንኳ በሕዝቡ ላይ ሠልጥነውባቸው ይጨቊኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንደዚያ አላደረግሁም።


በስውር አድልዎ ብታደርጉ በእውነት እግዚአብሔር ይገሥጻችኋል።


ሁሉም የእጁ ሥራዎች ስለ ሆኑ፤ እርሱ ለመኳንንቱ አያደላም ባለጸጋውን ከድኻው አይለይም።


እግዚአብሔር ፍርድን ከቶ አያጣምምም፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ሁልጊዜ ትክክለኛውን ነገር ያደርጋል።


“እስከ መቼ ትክክል ያልሆነ ፍርድ ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼ ለክፉዎች ታዳላላችሁ?


ሰዎች ትክክለኛ የሆነውን ነገር እንዳያዩ ዐይናቸውን ስለሚያሳውርና የንጹሕ ሰዎችንም ፍርድ ስለሚያጣምም ጉቦ አትቀበል።


በእውነትና በትክክል የሚናገሩ፥ በግፍ የሚገኝን ትርፍ የሚጸየፉ፥ ጉቦን ከመቀበል ይልቅ የሚያስወግዱ፥ ስለ ነፍስ ግድያ መስማት የማይፈልጉና፥ ክፉ ነገርን ከማየት ዐይኖቻቸውን የሚጨፍኑ፥


እጆቻቸው ክፉ ነገርን ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ባለ ሥልጣኑና ዳኛው ጉቦ ይጠይቃሉ፤ ኀይለኛ ፍላጎቱን በግዴታ ተግባራዊ ያስደርጋል፤ በዚህም ዐይነት ሁሉም ፍርድን ያጣምማሉ።


የእነርሱንም ደቀ መዛሙርት ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ወደ ኢየሱስ ልከው፥ “መምህር ሆይ! አንተ እውነተኛ መሆንህንና የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፤ ሰውንም በመፍራት የምታደርገው ነገር የለም፤ ለሰውም አታዳላም” ካሉት በኋላ፥ እንዲህ ብለው ጠየቁት።


ጴጥሮስ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፦ “በእውነት እግዚአብሔር ሰውን ከሰው እንደማያበላልጥ አስተዋልኩ፤


እግዚአብሔር በሰዎች መካከል አያዳላም።


እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ያዳላል ማለት እንችላለን? እግዚአብሔር ያዳላል ማለትስ ከቶ አንችልም!


እነዚህ መሪዎች መስለው የሚታዩት ግን እግዚአብሔር የሰውን ፊት አይቶ ስለማያዳላ ስለ እነርሱ የቀድሞ ማንነት ግድ የለኝም፤ እነዚህ መሪዎች የተባሉት እኔ በማበሥረው የምሥራች ቃል ላይ ምንም አዲስ ነገር አልጨመሩም።


እናንተም ጌቶች ሆይ! ለሰው ፊት የማያዳላ የእናንተና የእነርሱ ጌታ በሰማይ እንዳለ በማስታወስ ዛቻችሁን ትታችሁ ለአገልጋዮቻችሁ መልካም አድርጉላቸው።


“እርሱ ምሽጋችን ነው፤ ሥራዎቹም ፍጹሞች ናቸው፤ መንገዶቹም ሁሉ የቀኑ ናቸው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፥ እርሱም ቀጥተኛና እውነተኛ ነው።


በእግዚአብሔር ዘንድ አድልዎ ስለሌለ ክፉ የሚሠራም ስለ ክፉ ሥራው ቅጣቱን ይቀበላል።


ለማንም ሳያዳላ ለያንዳንዱ እንደየሥራው የሚፈርደውን እግዚአብሔርን “አባታችን” ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ በዚህ ዓለም በእንግድነት መጻተኞች ሆናችሁ ስትኖሩ እርሱን በመፍራት ኑሩ።


ጥንዱንም በሬዎች ወስዶ ቈራረጣቸው፤ የሥጋውንም ቊራጭ ሁሉ አስይዞ “ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ ወደ ጦርነት የማይወጣ ሰው ቢኖር በሬዎቹ እንደዚህ ይቈራረጡበታል!” ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር መልእክተኞችን ወደ መላው የእስራኤል ምድር ላከ። በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈራ፤ አንድም ሰው ሳይቀር ሁሉም በአንድነት ወጡ።


跟着我们:

广告


广告