Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 18:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ መታውና “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ከዚያም የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ ወጥቶ ሚክያስን በጥፊ መታውና፣ “ለመሆኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በየት በኩል ዐልፎኝ ነው አንተን ያናገረህ?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የክንዓናም ልጅ ሴዴቅያስ ቀረበ፥ ሚክያስንም በጥፊ መታውና እንዲህ አለ፦ “የጌታ መንፈስ ከአንተ ጋር ለመነጋገር በምን ዓይነት መንገድ ከእኔ አለፈ?”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የካ​ህ​ና​ንም ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ ቀረበ፤ ሚክ​ያ​ስ​ንም በጥፊ መታ​ውና፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ከአ​ንተ ጋር ይና​ገር ዘንድ በምን መን​ገድ ከእኔ አለፈ?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የክንዓናም ልጅ ሴዴቅያስ ቀረበ፤ ሚክያስንም በጥፊ መታውና “የእግዚአብሔር መንፈስ ከአንተ ጋር ይናገር ዘንድ በምን መንገድ ከእኔ አለፈ?” አለ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 18:23
13 交叉引用  

ከእነርሱም አንዱ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ከብረት ቀንዶችን ሠርቶ አክዓብን “እግዚአብሔር ‘በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’ ይልሃል” አለው።


ሚክያስም “ወደ ጓዳ ሄደህ በምትሸሸግበት ጊዜ ታገኘዋለህ” ሲል መለሰለት።


ተይዤ እንድደበደብ አዘዘ፤ ከቤተ መቅደሱም በላይኛው በኩል ባለው በብንያም የቅጽር በር በእግር ግንድ እንድታሰር አደረገ።


ለሚመታው ጒንጩን ይስጥ፤ ስድብንም ይቀበል።


“አንቺ የወታደር ከተማ ሠራዊትሽን አሰልፊ! ከበባው በእኛ ላይ ተጠናክሮአል፤ የእስራኤልንም መሪ ጒንጩ ላይ በበትር ይመቱታል።”


አንዳንዶችም ምራቃቸውን እንትፍ ይሉበት ጀመር፤ ዐይኑንም በጨርቅ ሸፍነው “አንተ ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደ መታህ ዕወቅ!” እያሉ በቡጢ ይመቱት ነበር። ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።


跟着我们:

广告


广告