Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 17:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከይሆሐናን ቀጥሎ በማዕርግ ሦስተኛ የሆነው የጦር መኰንን የዚክሪ ልጅ ዐማሥያ ነበር፤ በእርሱም ሥር ሁለት መቶ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር አገልግሎት የለየ የጦር አዛዥ ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያ ቀጥሎም ለእግዚአብሔር አገልግሎት በፈቃደኛነት ራሱን የሰጠው የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከሁለት መቶ ሺሕ ተዋጊዎች ጋራ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከእርሱም በኋላ በፈቃዱ ራሱን ለጌታ የቀደሰ የዝክሪ ልጅ ዓማስያ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከእ​ር​ሱም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግል የዝ​ክሪ ልጅ ማስ​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከእርሱም በኋላ በፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር የቀደሰ የዝክሪ ልጅ ዓማስያ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 17:16
10 交叉引用  

“ይህን ስጦታ በፈቃደኛነት መስጠት እንችል ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው? ሁሉ ነገር ከአንተ የተቀበልነው ስጦታ ነው፤ እነሆ የአንተ የነበረውንም መልሰን ሰጥተንሃል፤


አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤


ሕዝቡ በፈቃዳቸውና በሙሉ ልብ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰጡ፤ እጅግ ብዙ ሀብት ገቢ በመሆኑም ደስ አላቸው፤ ንጉሥ ዳዊትም ከመጠን በላይ ደስ ተሰኘ።


ከእርሱም ቀጥሎ በማዕርግ ሁለተኛ የሆነው የሆሐናን ተብሎ የሚጠራ የጦር አዛዥ ነበር፤ በእርሱም ሥር ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤


ከብንያም ነገድ ለተመለመሉት ወታደሮች ዋና አዛዥ ኤሊያዳዕ ተብሎ የሚጠራ ጀግና ወታደር ነበር፤ በእርሱም ሥር ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤


መግዛት በምትጀምርበት ቀን ሕዝብህ ይገዙልሃል፤ የተቀደሰውን መጐናጸፊያ ደርበህ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት እንደ ጠል ወለድኩህ።


ለመስጠት መልካም ፈቃድ ካለ የሰው ልግሥና ተቀባይነት የሚያገኘው ባለው መጠን ሲሰጥ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለም።


መሪዎች እስራኤልን ስለ መሩ፥ ሕዝቡም በፈቃደኛነት ራሱን ስላቀረበ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


ልቤ ከእስራኤል የጦር አዛዦች ጋር ነው፤ እንዲሁም ደስ ብሎአቸው በበጎ ፈቃድ ከተነሣሡት ጋር ነው፤ እግዚአብሔር ይመስገን!


跟着我们:

广告


广告