Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 17:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከይሁዳ ነገድ ለተመለመሉት ወታደሮች አዛዥ ዐድና ተብሎ የሚጠራ የጦር መኰንን ነበር፤ በእርሱም ሥር ሦስት መቶ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እነርሱም በየቤተ ሰቦቻቸው ሲመዘገቡ እንደሚከተለው ነው፤ ከይሁዳ የየሻለቃው አዛዦች፣ አዛዡ ዓድና ከሦስት መቶ ሺሕ ተዋጊዎች ጋራ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ቁጥራቸውም እንደ አባቶቻቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይሁዳ ሻለቆች አለቃው ዓድና፥ ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ቍጥ​ራ​ቸ​ውም እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይ​ሁዳ ሻለ​ቆች አለ​ቃው ዓድ​ናስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ቍጥራቸውም እንደ አባቶቻቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይሁዳ ሻለቆች አለቃው ዓድና፥ ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 17:14
11 交叉引用  

ዘርህን አበዛዋለሁ፤ ታላቅ ሕዝብም ይሆናል፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎችም በረከት ትሆናለህ።


ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ የምድር አሸዋ ሊቈጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር እንዲሁ ሊቈጠር የማይቻል ይሆናል።


ቀጥሎም እግዚአብሔር አብራምን ወደ ውጪ አወጣውና “ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ከዋክብትን መቊጠር ትችል እንደሆን ሞክር፤ እንግዲህ የአንተም ዘሮች እንደዚህ ይበዛሉ” አለው።


ንጉሥ ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች የተውጣጡ አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ምርጥ ወታደሮችን ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት የእስራኤልን ነገዶች ወግቶ ግዛቱን እንደገና በቊጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዐቅዶ ስለ ነበር ነው።


በዚህ ጊዜ አቢያ አራት መቶ ሺህ ሠራዊት ይዞ ሲዘምት፥ ኢዮርብዓም ደግሞ ስምንት መቶ ሺህ ወታደሮችን አሰለፈ።


ንጉሥ አሳ ታላላቅ ጋሻና ጦር የታጠቁ ሦስት መቶ ሺህ ሠራዊት ከይሁዳ፥ ታናናሽ ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ ሠራዊት ከብንያም ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ በሚገባ የሠለጠኑ ጀግኖች ወታደሮች ነበሩ።


ከእርሱም ቀጥሎ በማዕርግ ሁለተኛ የሆነው የሆሐናን ተብሎ የሚጠራ የጦር አዛዥ ነበር፤ በእርሱም ሥር ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤


በእነርሱም ሥልጣን ሥር የንጉሡን ጠላቶች ለመመከት በቂ ችሎታ ያላቸው ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ጀግኖች ወታደሮች ነበሩ፤


ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ ማኅበሩን ሁሉ በአንድነት ሰብስበው በየነገዱና በየቤተሰቡ ከመደቡ በኋላ የሕዝብ ቈጠራ አደረጉ፤ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ስማቸው እየተመዘገበ ተቈጠሩ።


“አንተና አሮን፥ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ በየነገዱና በየቤተሰቡ ኻያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነውን እያንዳንዱን ወንድ አንድ በአንድ እየቈጠራችሁ መዝግቡ።


跟着我们:

广告


广告