Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 13:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ሚካያ ተብላ የምትጠራ የጊብዓ ከተማ ተወላጅ የሆነ የኡሪኤል ልጅ ነበረች። በአቢያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ተነሥቶ ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ዓመት ገዛ። እናቱ ሚካያ ትባላለች፤ እርሷም የጊብዓ ተወላጅ የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓምም መካከል ጦርነት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሦስት ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም ሚካያ ነበረ፥ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሦስት ዓመ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገሠ፤ የእ​ና​ቱም ስም መዓካ ነበረ፤ የገ​ባ​ዖን ሰው የኡ​ር​ኤል ልጅ ነበ​ረች። በአ​ብ​ያና በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መካ​ከ​ልም ሰልፍ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሦስት ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም ሚካያ ነበረ፤ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 13:2
11 交叉引用  

ንጉሥ ኢዮርብዓም ያደረጋቸው ሌሎች ነገሮች ሁሉ፥ የተዋጋቸው ጦርነቶችና አገዛዙም እንዴት እንደ ነበር ሁሉም ነገር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።


ኢዮርብዓም ንጉሥ ሆኖ ኻያ ሁለት ዓመት ከገዛ በኋላ ሞቶ ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ልጁ ናዳብ ተተክቶ ነገሠ።


መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ማዕካ ተብላ የምትጠራ የአቤሴሎም ልጅ ነበረች፤


ቈየት ብሎም ሮብዓም፥ ማዕካ ተብላ የምትጠራውን የአቤሴሎምን ልጅ አግብቶ አቢያ፥ ዓታይ፥ ዚዛና ሼሎሚት ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ።


ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ነገር ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንዲሁም የቤተሰቡ ታሪክ በነቢዩ ሸማዕያና በነቢዩ ዒዶ ታሪክ መጻሕፍት ተመዝግቦ ይገኛል፤ ሮብዓምና ኢዮርብዓም ባለማቋረጥ ዘወትር ይዋጉ ነበር፤


በዚህ ጊዜ አቢያ አራት መቶ ሺህ ሠራዊት ይዞ ሲዘምት፥ ኢዮርብዓም ደግሞ ስምንት መቶ ሺህ ወታደሮችን አሰለፈ።


ጼላዕ፥ ኤሌፍ፥ ኢያቡስ (ኢየሩሳሌም) ጊብዓና ቂርያትይዓሪም ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ አራት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙትን ትናንሽ ከተሞችንም ይጨምራሉ። እንግዲህ የብንያም ነገድ በየወገኖቻቸው የተቀበሉት ርስት ይህ ነው።


ስለዚህ ኢየሩሳሌምን አልፈው ጒዞአቸውን ወደፊት ቀጠሉ፤ በብንያም ግዛት በምትገኘው በጊብዓ ሲደርሱ ፀሐይ ጠለቀች፤


በዚያም ተቀምጠው ሳሉ በእርሻ ቦታ የቀን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ቤቱ የሚመለስ አንድ ሽማግሌ በአጠገባቸው አለፈ፤ ይህ ሰው አስቀድሞ ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር የመጣ ሲሆን፥ አሁን ግን የሚኖረው በጊብዓ ነበር፤ በዚያ የሚኖሩት ሌሎቹ ሰዎች ግን ከብንያም ነገድ የተወለዱ ናቸው፤


ሳኦልም በጊብዓ ወደሚገኘው ቤቱ ተመልሶ ሄደ፤ እግዚአብሔር ልባቸውን ያነሣሣው ኀያላንም ሳኦልን ተከትለው ሄዱ፤


跟着我们:

广告


广告