2 ዜና መዋዕል 12:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ነገር ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንዲሁም የቤተሰቡ ታሪክ በነቢዩ ሸማዕያና በነቢዩ ዒዶ ታሪክ መጻሕፍት ተመዝግቦ ይገኛል፤ ሮብዓምና ኢዮርብዓም ባለማቋረጥ ዘወትር ይዋጉ ነበር፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ሮብዓም በዘመነ መንግሥቱ ያከናወናቸው ተግባሮች ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ነቢዩ ሸማያ በጻፈው የታሪክ መዝገብና ባለራእዩ አዶ በዘገበው የትውልድ ሐረግ ታሪክ የሚገኝ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ ሸማያና በባለ ራእዩ በአዶ የትውልድ ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከልም በዘመናቸው ሁሉ ጦርነት ነበረ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር እነሆ፥ በነቢዩ ሰማያና በባለ ራእዩ በአዶ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ሮብዓምም ከኢዮርብዓም ጋር በዘመኑ ሁሉ ይዋጋ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ ሸማያና በባለ ራዕዩ በአዶ የትውልድ ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከልም በዘመናቸው ሁሉ ሰልፍ ነበረ። 参见章节 |