Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 11:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ንጉሥ ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች የተውጣጡ አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ምርጥ ወታደሮችን ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት የእስራኤልን ነገዶች ወግቶ ግዛቱን እንደገና በቊጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዐቅዶ ስለ ነበር ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ፣ የእስራኤልን ቤት ወግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም እንዲመልሱ ከይሁዳና ከብንያም ቤት አንድ መቶ ሰማንያ ሺሕ ወታደሮች ሰበሰበ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሮብዓምም ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ እስራኤልን ወግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም ለመመለስ ከይሁዳና ከብንያም ቤት የተመረጡትን አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ወታደሮች ሰበሰበ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሮብ​ዓ​ምም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመጣ ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ልን ወግ​ተው መን​ግ​ሥ​ቱን ወደ ሮብ​ዓም ይመ​ልሱ ዘንድ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ቤት የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አንድ መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞች ጐል​ማ​ሶ​ችን ሰበ​ሰበ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሮብዓምም ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ እስራኤልን ወግተው መንግስቱን ወደ ሮብዓም ይመልሱ ዘንድ ከይሁዳና ከብንያም ቤት የተመረጡትን አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰልፈኞች ሰዎች ሰበሰበ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 11:1
6 交叉引用  

ስለዚህ ለራሴ ምንም ነገር አልወስድም፤ የእኔ ሰዎች የያዙትን እንዲወስዱ እስማማለሁ፤ እንዲሁም የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቼ ዐኔር፥ ኤሽኮልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።”


ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ፤ በዚያም እርሱን ለማንገሥ የፈለጉ በእስራኤል ሰሜናዊ ግዛት የሚኖሩ እስራኤላውያን ተሰብስበው ይጠብቁት ነበር።


እግዚአብሔር የአሕዛብን ዕቅድ እንዳይሳካ ያደርጋል፤ የሕዝቦችንም ዓላማ ዋጋቢስ ያደርጋል።


ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፤ አርበኛም በከፍተኛ ኀይሉ አያመልጥም።


跟着我们:

广告


广告