2 ዜና መዋዕል 10:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የአባቱ የሰሎሞን አማካሪዎች የነበሩትን ሽማግሌዎች በአንድነት ሰብስቦ “እንግዲህ ለዚህ ሕዝብ መልስ መስጠት እንድችል ምን ትመክሩኛላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ከዚያም ንጉሡ ሮብዓም አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ ካገለገሉት ሽማግሌዎች ጋራ ተማከረ፤ “ለዚህ ሕዝብ ምን መልስ እንድሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ንጉሡም ሮብዓም፦ “ለዚህ ሕዝብ እንድመልስለት የምትመክሩኝ ነገር ምንድነው?” ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወት ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ንጉሡም ሮብዓም፥ “ለዚህ ሕዝብ እመልስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድን ነው?” ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወት ሳለ በፊቱ ይቆሙ የነበሩትን ሽማግሌዎች ሰበሰበ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ንጉሡም ሮብዓም “ለዚህ ሕዝብ እመልስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው?” ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወት ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ። 参见章节 |