Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 10:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “አባትህ ቀንበር አክዶብን ነበር፤ አንተ ግን አቅልልልን ለሚሉህ ሰዎች የምትሰጣቸው መልስ ይህ ነው፦ ‘የእኔ ታናሽ ጣት ከአባቴ ወገብ ይበልጥ ትወፍራለች፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ዐብሮ አደጎቹም ወጣቶች እንዲህ አሉት፤ “ ‘አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚሉህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ይልቅ ትወፍራለች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከእርሱም ጋር ያደጉት ብላቴኖች እንዲህ በላቸው ብለው ተናገሩት፦ “ ‘አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር፥ አንተ ግን አቅልልልን’ ለሚሉህ ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ ‘ታናሽቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከእ​ር​ሱም ጋር ያደ​ጉት ብላ​ቴ​ኖች፥ “አባ​ትህ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ብን ነበር፤ አንተ ግን አቅ​ል​ል​ልን ለሚ​ሉህ ሕዝብ፦ ታና​ሺቱ ጣቴ ከአ​ባቴ ወገብ ትወ​ፍ​ራ​ለች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከእርሱም ጋር ያደጉት ብላቴኖች “‘አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር፤ አንተ ግን አቅልልልን፤’ ለሚሉህ ሕዝብ ‘ታናሽቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች፤

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 10:10
14 交叉引用  

ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ፤ በዚያም እርሱን ለማንገሥ የፈለጉ በእስራኤል ሰሜናዊ ግዛት የሚኖሩ እስራኤላውያን ተሰብስበው ይጠብቁት ነበር።


አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ ይኸውም አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ።’ ”


“ላደርገው ስለሚገባኝ ነገር ምን ትመክሩኛላችሁ? የአገዛዝ ቀንበር እንዳቀልላቸው ለጠየቁኝስ ሰዎች ምን መልስ ልስጣቸው?” ሲል ጠየቃቸው።


ጠቢባን በሚቻላቸው ዘዴ ሁሉ ዕውቀትን ያከማቻሉ፤ ሞኞች በሚናገሩበት ጊዜ ግን ጥፋት መምጣቱ አይቀርም።


አስተዋይ ሰዎች ለሚሠሩት ሥራ አስቀድመው ዕቅድ ያወጣሉ፤ ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ግን አላዋቂነታቸውን ይገልጣሉ።


ብልኆች እግዚአብሔርን ስለሚፈሩ ከክፉ ነገር ለመራቅ ይጠነቀቃሉ፤ ሞኞች ግን ከአደጋ የማይጠነቀቁ ችኲሎች ናቸው።


ልጄ ሆይ! ምክሬን ባትሰማ የምታውቀውን ትምህርት እንኳ በቶሎ ረስተህ ትሳሳታለህ።


ሰው በጥበቡ፥ በአስተዋይነቱና በዕቅዱ በእግዚአብሔር ላይ መነሣት አይችልም።


ስስታም ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው ግን ይበለጽጋል።


ትምክሕተኛነት ወደ ውድቀት ያደርስሃል፤ ትሑት ከሆንክ ግን ትከበራለህ።


跟着我们:

广告


广告