Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሰሎሞንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንተ ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ ፍቅርህን ባለማቋረጥ አሳይተኸዋል፤ አሁንም እኔ በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ አድርገሃል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሰሎሞን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ ቸርነትን አሳይተኸዋል፤ እኔንም በእግሩ ተክተህ አንግሠኸኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሰሎሞንም ጌታን እንዲህ አለው፦ “ለአባቴ ለዳዊት ታላቅና ጽኑ ፍቅር አሳይተኸዋል፥ በእርሱም ፋንታ አንግሠኸኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ከአ​ባቴ ከዳ​ዊት ጋር ታላቅ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ገ​ሃል፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሰሎሞንም እግዚአብሔርን አለው “ከአባቴ ከዳዊት ጋር ታላቅ ምሕረት አድርገሃል፤ በእርሱም ፋንታ አንግሠኸኛል።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 1:8
13 交叉引用  

እርሱ ላነገሠው ንጉሥ ድልን ያጐናጽፈዋል፤ እርሱ ከቀባውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ያሳየዋል፤ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘለዓለም ይህን ያደርጋል።


ሰሎሞንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አገልጋይህ የነበረው አባቴ ዳዊት ደግ፥ ታማኝና ቅን ሰው በመሆኑ ጽኑ ፍቅርህን ስታሳየው ኖረሃል፤ ዛሬም በእርሱ እግር ተተክቶ በዙፋኑ የሚቀመጥ ልጅ በመስጠት ታላቅና ጽኑ የሆነውን የማያቋርጥ ፍቅርህን ገልጠህለታል፥


ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ድንኳን ሄደ፤ ተቀምጦም እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እኔ ይህን ሁሉ ነገር ታደርግልኝ ዘንድ እኔ ማነኝ? ቤተሰቤስ ምንድን ነው?


ለእኔም ብዙ ወንዶች ልጆችን ሰጠኝ፤ ነገር ግን የሚቀጥለው የእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ የመረጠው ልጄን ሰሎሞንን ነው።”


በዚህ ዐይነት ሰሎሞን በአባቱ እግር ተተክቶ እግዚአብሔር ባጸናው ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ እርሱም ሁሉ ነገር የተሳካለት ንጉሥ ሆነ፤ መላውም የእስራኤል ሕዝብ ታዘዙለት፤


ብዙ ሀብትና ክብር ካገኘም በኋላ በዕድሜ እጅግ ሸምግሎ ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሰሎሞን ነገሠ፤


ለእኔ የምታሳየው ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እንዴት ታላቅ ነው! ወደ ሲኦል ጥልቀት ከመውረድ አዳንከኝ።


ጌታ ሆይ! የቀድሞዎቹ የፍቅርህ ማረጋገጫዎች የት አሉ? ለዳዊት የሰጠኸውስ የተስፋ ቃል የት ነው?


“ጆሮአችሁን አዘንብላችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ቃሌን አድምጡ፤ ዳዊትን እንደ ወደድኩት እናንተን በታማኝነት ለመውደድ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።


跟着我们:

广告


广告