Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 1:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በገባዖን ወደሚገኘው ኰረብታማ የማምለኪያ ስፍራ አብረውት እንዲሄዱ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወደዚያ የሄዱበትም ምክንያት፥ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው፥ እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን በዚያው በገባዖን ስለሚገኝ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የአምላክ የመገናኛ ድንኳን በዚያ ስለ ነበር፣ ሰሎሞንና መላው ጉባኤ በገባዖን ወዳለው ኰረብታ ሄዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር ጉባኤው ሁሉ የጌታ ባርያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው መገናኛ ድንኳን በዚያ ነበረና በገባዖን ወዳለው ወደ ኮረብታማው ስፍራ ሄዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ በም​ድረ በዳ የሠ​ራው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ስ​ክር ድን​ኳን በዚያ ነበ​ረና በገ​ባ​ዖን ወዳ​ለው የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ሄዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር ጉባኤው ሁሉ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር መገናኛ ድንኳን በዚያ ነበረና በገባዖን ወዳለው የኮረብታው መስገጃ ሄዱ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 1:3
12 交叉引用  

ወደ ቤተ መቅደስ አገቡት፤ እንዲሁም ሌዋውያንና ካህናት የእግዚአብሔር መገኛ ድንኳንና በድንኳኑም ውስጥ የነበሩትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አምጥተው ወደ ቤተ መቅደስ አገቡ።


ካህኑን ሳዶቅንና የእርሱ ወገኖች የሆኑትን ሌሎቹን ካህናት በገባዖን ባለው እግዚአብሔር በሚመለክበት ድንኳን ለሚደረገው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ኀላፊዎች እንዲሆኑ አደረጋቸው።


ሙሴ በበረሓ የሠራው እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳንና መሥዋዕት ይቀርብበት የነበረው መሠዊያ እስከዚህ ጊዜ ድረስ በገባዖን በሚገኘው የማምለኪያ ስፍራ ይገኛሉ፤


ሰሎሞን እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን ካለበት፥ በገባዖን ከሚገኘው ኰረብታማ ማምለኪያ ስፍራ ተነሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ በእስራኤል ላይ ነገሠ።


ሥራውን ከሚያከናውኑት መካከል እጅግ ጥበበኞች የነበሩት የተቀደሰውን ድንኳን ሠሩ፤ እነርሱም ድንኳኑን ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተሉ፥ የኪሩቤል ሥዕል ከተጠለፈባቸው ዐሥር የበፍታ መጋረጃዎች ሠሩት።


“የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን የመገናኛውን ድንኳን ትከል።


ከዚህ በኋላ ድንኳኑ በደመና ተሸፈነ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ድንኳኑን ሞላው።


ከመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሆኖ እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው፤ እንዲህ ብሎም አዘዘው፥


ስለዚህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞአብ ምድር ሳለ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት በዚያ ሞተ።


የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በዐይ ከተማዎች ላይ ያደረገውን ሁሉ ስለ ሰሙ፤


跟着我们:

广告


广告