Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሰሎሞን በአንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና በዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች የተጠናከረ ሠራዊትን አደራጀ፤ ከእነርሱም ከፊሉን በኢየሩሳሌም፥ የቀረውን ደግሞ በሌሎች ልዩ ልዩ ከተሞች በመመደብ በዚያው እንዲኖሩ አደረገ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሰሎሞን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺሕ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺሕ ፈረሶች ነበሩት፤ እነርሱንም በሠረገላ ከተሞችና ንጉሡ ባለበት በኢየሩሳሌም ከተማ አኖራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሰሎሞንም ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን ሰበሰበ፥ አንድ ሺህም አራት መቶ ሰረገሎች፥ ዐሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሰረገሎች ከተሞችና ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሰሎ​ሞ​ንም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሰበ​ሰበ፤ አንድ ሺህ አራት መቶ ሰረ​ገ​ሎች፥ ዐሥራ ሁለት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎች ከተ​ሞ​ችም አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው። ሕዝ​ቡም ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሰሎሞንም ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ሰበሰበ፤ አንድ ሺህ አራት መቶም ሠረገሎች፥ ዐሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሠረገሎች ከተሞችና ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 1:14
8 交叉引用  

ንጉሥ ሰሎሞን ሁለት መቶ ታላላቅ ጋሻዎችን አሠርቶ እያንዳንዱን ጋሻ በሰባት ኪሎ ያኽል ወርቅ አስለበጠው፤


ሰሎሞን ሠረገላ የሚስቡ አርባ ሺህ ቅልብ ፈረሶችና ለጦርነት የሚያገለግሉ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት፤


ስለዚህ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት የሚቈርጡ ሰዎችን ወደ ሊባኖስ ላክልኝ፤ የእኔም ሰዎች ከእነርሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ አደርጋለሁ፤ ለሰዎችህም አንተ የምትወስነውን ደመወዝ እከፍላለሁ፤ አንተ እንደምታውቀው የእኔ ሰዎች ስለ ዛፍ አቈራረጥ የአንተን ሰዎች ያኽል ዕውቀት የላቸውም።”


እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው፥ ከተሞችን ከተመ፤ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ።


የባዕላት ከተማ፥ ስንቅና ትጥቅ የሚያስቀምጥባቸው ከተሞች ሁሉ፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚኖሩባቸው ከተሞች፤ በዚህም ዐይነት ሰሎሞን በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በእርሱ አስተዳደር ባለው ግዛት በሙሉ ሊሠራ ያቀዳቸውን የግንባታ ሥራዎች ሁሉ ፈጸመ።


ንጉሥ ሰሎሞን ለሠረገሎቹና ለፈረሶቹ አራት ሺህ ጋጣዎች፥ እንዲሁም ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሉን በኢየሩሳሌም፥ የቀሩትም ደግሞ በሌሎች ልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ፤


ያም ንጉሥ ለሠራዊቱ ብዙ ፈረሶች ያሉት መሆን የለበትም፤ እግዚአብሔር ሕዝቡ ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ስለ አዘዘ ፈረሶችን ለመግዛት ወደ እዚያ ሰዎችን አይላክ።


跟着我们:

广告


广告