1 ጢሞቴዎስ 6:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ጌቶቻቸው አማኞች የሆኑ አገልጋዮች በጌታ ኢየሱስ ወንድሞቻቸው ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ይልቅስ ከአገልግሎታቸው ጥቅም የሚያገኙ ጌቶቻቸው አማኞችና የተወደዱ ወንድሞቻቸው ስለ ሆኑ ከበፊት ይበልጥ ያገልግሉአቸው። አንተም ማስተማርና መምከር የሚገባህ ይህን ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 የሚያምኑ ጌቶች ያሏቸውም፣ ወንድሞች ስለ ሆኑ የሚገባቸውን ክብር አይንፈጓቸው፤ ይልቁንም በአገልግሎታቸው የሚጠቀሙ አማኞችና ወዳጆቻቸው ስለ ሆኑ የበለጠ ሊያገለግሏቸው ይገባል። እነዚህን ነገሮች አስተምር፤ ምከርም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቋቸው፤ ይልቁንስ ከበፊት ይልቅ ያገልግሏቸው ምክንያቱም በመልካም ሥራቸው የሚጠቀሙት አማኞችና ወዳጆቻቸው ናቸውና። እነዚህን ነገርች አስተምርና ምከር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፥ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ። 参见章节 |