Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 8:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ይሁን እንጂ ሕዝቡ ሳሙኤል ለነገራቸው ቃል ሁሉ ዋጋ አልሰጡትም፤ ይልቁንም “እንደዚህ አይደለም! እኛ ንጉሥ እንዲኖረን እንፈልጋለን፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን መስማት እንቢ በማለት፤ እንዲህ አሉ፤ “አይሆንም፤ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን መስማት እምቢ በማለት፥ እንዲህ አሉ፦ “አይሆንም፤ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሕዝቡ ግን የሳ​ሙ​ኤ​ልን ነገር ይሰሙ ዘንድ እንቢ አሉ፥ “እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሕዝቡ ግን የሳሙኤልን ነገር ይሰማ ዘንድ እንቢ አለ፦ እንዲህ አይሁን፥ ነገር ግን ንጉሥ ይሁንልን፥

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 8:19
9 交叉引用  

የይሁዳ ሰዎች ግን ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ይልቁንም ምናሴ እስራኤላውያን ወደፊት እየገፉ ሲመጡ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸው ሕዝቦች ይፈጽሙት ከነበረው ይበልጥ ወደ ከፋ ኃጢአት መራቸው።


“ሕዝቤ ግን እኔን አልሰማኝም፤ እስራኤል አልታዘዘልኝም።


ስለዚህ በልበ ደንዳናነታቸው አካሄድ እንዲሄዱ፥ የፈለጉትንም ነገር እንዲያደርጉ ተውኳቸው።


ስጠራ ማንም ስላልመለሰልኝ፥ ስናገር ማንም ስላላዳመጠኝ ነገር በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጉና የማያስደስተኝን ስለ መረጡ እኔም በእነርሱ ላይ ቅጣት አመጣባቸዋለሁ።”


“አንተ በእግዚአብሔር ስም የተናገርከውን ሁሉ መስማት አንፈልግም፤


እናንተ ይህን ሁሉ በደል ፈጸማችሁ፤ ደጋግሜ ብነግራችሁም አናዳምጥም ብላችኋል፤ በጠራኋችሁም ጊዜ መልስ አልሰጣችሁኝም።


ስለዚህም ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሕዝቤ አንተ ምን እንደምትናገር ለማዳመጥ ብቻ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የምትነግራቸውን ሁሉ አይፈጽሙም፤ የምትናገረውን ቃል የሚወዱት መስለው ይታያሉ፤ ነገር ግን ከበዝባዥነታቸው አይመለሱም፤


“እግዚአብሔር አምላክህ ወደሚሰጥህ ምድር በመግባት ምድሩን ወርሰህ ከተደላደልክ በኋላ በዙሪያዬ እንዳሉት ሕዝቦች ንጉሥ ላንግሥ ብትል፥


እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ንጉሣችሁ ሆኖ ሳለ የአሞን ንጉሥ ናዖስ በእናንተ ላይ መነሣቱን ባያችሁ ጊዜ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ።


跟着我们:

广告


广告