Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 7:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በየዓመቱም ወደ ቤትኤል፥ ጌልጌላና ምጽጳ እየሄደ በእነዚህ ስፍራዎች ይፈርድ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በየዓመቱ በቤቴል፣ በጌልገላና በምጽጳ እየተዘዋወረ፣ በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በየዓመቱ በቤቴል፥ በጌልጌላና በምጽጳ እየተዘዋወረ፥ በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌል​ጌ​ላና ወደ መሴፋ ይዞር ነበር፤ በእ​ነ​ዚ​ያም በተ​ቀ​ደሱ ስፍ​ራ​ዎች ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በየዓመቱም ወደ ቤቴል ወደ ጌልገላ ወደ ምጽጳም ይዞር ነበር፥ በእነዚያም ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 7:16
15 交叉引用  

ያንንም ስፍራ “ቤትኤል” ብሎ ሰየመው፤ ይህ ስፍራ ከዚያ በፊት ሎዛ እየተባለ ይጠራ ነበር።


ያዕቆብ አብረውት ከነበሩት ሰዎች ጋር ሆኖ ወደ ሎዛ ደረሰ፤ ሎዛ ቤትኤል ተብላ የምትጠራው በከነዓን ምድር የምትገኝ ስፍራ ናት።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ፍርድ የምሰጥበትን ጊዜ ወስኛለሁ፤ በዚያን ጊዜ በትክክል እፈርዳለሁ።


“ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ! እናንተም የእስራኤል ሕዝብ አስተውሉ! እናንተም ንጉሣውያን ቤተሰብ ይህን አድምጡ! እነሆ ፍርድ በእናንተ ላይ መጥቶአል፤ በምጽጳ እንደ ወጥመድ፥ በታቦርም እንደ ተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።


ወደ ቤርሳቤህ አትሂዱ፤ ቤቴል ፈራርሳ እንዳልነበረች ስለምትሆን በጌልገላ የሚኖሩ ሕዝቦችም ስደት ስለ ተፈረደባቸው ወደ ቤቴልም ሆነ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ።”


ምጽጳ፥ ከፊራ፥ ሞጻ፥


እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ ባለው ሜዳ በጌልገላ ሰፍረው ሳሉ፥ ከወሩ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የፋሲካን በዓል አከበሩ፤


እግዚአብሔር ኢያሱን፦ “እነሆ፥ ዛሬ እኔ ከእናንተ ላይ የግብጽን ነውር አስወግጄላችኋለሁ” አለው። ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ጌልጌላ ተብሎ ይጠራል።


በሠላሳ አህዮች ላይ ተቀምጠው የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በገለዓድ ምድር ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው፤ እነዚህም ከተሞች እስከ ዛሬ የያኢር መንደሮች ተብለው ይጠራሉ፤


ዓብዶን በሰባ አህዮች ላይ ተቀምጠው የሚጋልቡ አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ የልጅ ልጆች ነበሩት፤ ዓብዶን ስምንት ዓመት የእስራኤል መሪ ሆነ።


እናንተ ኮርቻ በተጫኑ በነጫጭ አህዮች ላይ ተቀምጣችሁ የምትጓዙ፥ እናንተ በምቹና በአማረ ግላስ ላይ የምትንደላቀቁ፥ እናንተ በእግር የምትንሸራሸሩ፥ ስለዚህ ነገር ተናገሩ።


ሳሙኤል ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ ወደ ምጽጳ ጠራ።


ሳሙኤልም “ሁላችንም ወደ ጌልጌላ እንሂድና ሳኦል ንጉሣችን መሆኑን እንደገና በይፋ እናረጋግጥ” አላቸው።


ከዚህም በኋላ ሳሙኤል “እኔ በዚያ ለእናንተ ወደ እግዚአብሔር ስለምጸልይላችሁ በምጽጳ ተሰብሰቡ” ብሎ ለእስራኤላውያን ሁሉ ጥሪ አደረገ።


跟着我们:

广告


广告