Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 31:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ጀግኖቻቸው በድንገት ተነሥተው በመገሥገሥ በሌሊት ወደ ቤትሻን ሄዱ፤ የሳኦልንና የልጆቹን አስከሬን ከከተማይቱ ቅጽር ግንብ ላይ አውርደው ወደ ያቤሽ በማምጣት አቃጠሉአቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ጀግኖቻቸው ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሙሉ ተጓዙ፤ የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከቤትሳን ግንብ ላይ አውርደው ወደ ኢያቢስ አምጥተው አቃጠሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጀግኖቻቸው ሁሉ በሌሊት ወደ ቤትሻን ሄዱ። የሳኦልንና የልጆቹንም ሬሳ ከግንቡ ላይ አውርደው ወደ ያቤሽ አምጥተው አቃጠሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የሳ​ኦ​ል​ንም ሬሳ፥ የልጁ የዮ​ና​ታ​ን​ንም ሬሳ ከቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አወ​ረዱ፤ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም አቃ​ጠ​ሉ​አ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ጀግኖች ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ፥ የሳኦልንም ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ከቤትሳን ቅጥር ላይ አወረዱ፥ ወደ ኢያቢስም መጡ፥ በዚያም አቃጠሉት።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 31:12
6 交叉引用  

ኀያላን የሆኑ ሰዎች ሄደው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ በመውሰድ ወደ ያቤሽ አመጡ፤ በዚያም በወርካ ዛፍ ሥር ከቀበሩአቸው በኋላ ሰባት ቀን በሙሉ ጾሙ።


ሬሳውም በልዩ ቅመማ ቅመምና በሽቶ ታሽቶ እርሱ ራሱ በዳዊት ከተማ ከአለት አስፈልፍሎ ባሠራው መቃብር ተቀበረ፤ ስለ ክብሩም ብዙ እንጨት ከምረው በማንደድ ታላቅ ለቅሶ አደረጉለት።


በሰላም ታርፋለህ፤ ከአንተ በፊት ነገሥታት የነበሩ የቀድሞ አባቶችህ በሞቱ ጊዜ ሕዝቡ ለክብራቸው እሳት ያነዱላቸው እንደ ነበር ለአንተም እንዲሁ እሳት ያነዱልሃል፤ ‘ወዮ ንጉሣችን፥’ እያሉም ያለቅሱልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ከሟቾቹ የአንዱ የቅርብ ዘመድ የሆነና ሥርዓተ ቀብሩን የሚፈጽም ሬሳውን ከቤት አውጥቶ ይወስዳል፤ በዚያን ጊዜ በቤት ውስጥ ያለውን አንድ ሰው ጠርቶ “ከአንተ ጋር የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ብሎ ይጠይቀዋል፤ ሰውየውም “ማንም የቀረ የለም!” ብሎ ይመልስለታል፤ ጠያቂውም “የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ስለማይገባን ዝም በል!” ይለዋል።


ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን የሳኦልን የጦር መሣሪያዎች ዐስታሮት ተብላ በምትጠራው ሴት አምላካቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖሩ። የሳኦልንም ሬሳ ቤትሻን ተብላ በምትጠራው ከተማ ቅጽር ግንብ ላይ በምስማር ቸነከሩት።


跟着我们:

广告


广告