Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 30:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዳዊትም ወጣቱን “የማን አገልጋይ ነህ? አመጣጥህስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቀው። ወጣቱም “እኔ ግብጻዊ የሆንኩ የአንድ ዐማሌቃዊ አገልጋይ ነኝ፤ ታምሜ ስለ ነበር ከሦስት ቀን በፊት ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዳዊትም፣ “አንተ የማን ነህ? የመጣኸውስ ከየት ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔ ግብጻዊ ስሆን፣ የአንድ አማሌቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦስት ቀን በፊት ታምሜ በነበረበት ጊዜ ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዳዊትም፥ “አንተ የማን ነህ? የመጣኸውስ ከየት ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔ ግብፃዊ ስሆን፥ የአንድ አማሌቃዊ አገልጋይ ነኝ፤ ከሦስት ቀን በፊት ታምሜ በነበረበት ጊዜ ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትም፥ “አንተ የማን ነህ? ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ያም ግብ​ፃዊ ብላ​ቴና፥ “እኔ የአ​ማ​ሌ​ቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦ​ስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበ​ርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትም፦ አንተ የማን ነህ? ከወዴት መጣህ? አለው። እርሱም፦ እኔ የአማሌቃዊ ባሪያ ግብጻዊ ብላቴና ነኝ፥ ከሦስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 30:13
9 交叉引用  

ዳዊትም ወሬውን ይዞ የመጣውን ያንን ወጣት “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “በሀገርህ ውስጥ በመጻተኛነት የሚኖር የዐማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት።


ዳዊትም “ከወዴት መጣህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “ከእስራኤላውያን ሰፈር አምልጬ የመጣሁ ነኝ” ሲል መለሰ።


ማን እንደ ሆንኩ በጠየቀኝ ጊዜም ዐማሌቃዊ መሆኔን ነገርኩት፤


ደግ ሰው ለቤቱ እንስሳት ይራራል፤ የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።


ስለዚህ ዮናስን “እስቲ ንገረን! ይህ ሁሉ አደጋ የመጣብን በማን ምክንያት ይመስልሃል? ለመሆኑ ሥራህ ምንድን ነው? ከወዴት መጣህ? አገርህስ የት ነው? የየትኛው ሕዝብ ወገን ነህ?” አሉት።


የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።


ደረቅ የበለስ ፍሬና ሁለት ጥፍጥፍ ዘቢብ አቀረቡለት፤ ወጣቱም ከተመገበ በኋላ እንደገና በረታ፤ ከዚያ በፊት ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እህል ውሃ አልቀመሰም ነበር።


ይህም ከመሆኑ በፊት በይሁዳ ደቡብ የምትገኘውን የከሪታውያንን ግዛትና የካሌብን ግዛት በመውረር ጺቅላግን አቃጥለናታል” ሲል መለሰለት።


跟着我们:

广告


广告