1 ሳሙኤል 28:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ሳኦል “ምንም ነገር አልቀምስም” ብሎ እምቢ አለ፤ ይሁን እንጂ ባለሟሎቹም እንዲመገብ አበረታቱት፤ በመጨረሻም “እሺ” ብሎ ከወደቀበት መሬት በመነሣት አልጋ ላይ ተቀመጠ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 እርሱም፣ “አልበላም” በማለት እንቢ አለ። ነገር ግን የራሱ ሰዎች ከሴትየዋ ጋራ ሆነው አጥበቀው ስለ ለመኑት ቃላቸውን ሰማ፤ ከመሬትም ተነሥቶ በዐልጋ ላይ ተቀመጠ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 እርሱም፥ “አልበላም” በማለት እምቢ አለ። ነገር ግን የራሱ ሰዎች ከሴትዮዋ ጋር ሆነው አጥበቀው ስለ ለመኑት ቃላቸውን ሰማ። ከመሬትም ተነሥቶ በአልጋ ላይ ተቀመጠ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 እርሱ ግን፥ “አልበላም” ብሎ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ብላቴኖቹና ሴቲቱ አስገደዱት፤ ቃላቸውንም ሰማ፤ ከምድርም ተነሥቶ በአልጋ ላይ ተቀመጠ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 እርሱ ግን፦ አልበላም ብሎ እንቢ አለ፥ ነገር ግን ባሪያዎቹና ሴቲቱ አስገደዱት፥ ቃላቸውንም ሰማ ከምድርም ተነሥቶ በአልጋ ላይ ተቀመጠ። 参见章节 |