Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 23:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዳዊትም ሳኦል ሊገድለው መምጣቱን ተመለከተ። ዳዊት በዚፍ አጠገብ ባለው ምድረ በዳ ውስጥ በሖሬሽ ይገኝ ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ዳዊት በዚፍ ምድረ በዳ ሖሬሽ በተባለ ቦታ ሳለ፣ ሳኦል ሊገድለው መምጣቱን አየ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዳዊት በዚፍ ምድረ በዳ ሖሬሽ በተባለ ቦታ ሳለ፥ ሳኦል ሊገድለው መምጣቱን አየ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዳዊ​ትም ሳኦል ሊፈ​ል​ገው እንደ ወጣ አየ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ዚፍ ምድረ በዳ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስጥ ይኖር ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዳዊትም ሳኦል ነፍሱን ሊፈልግ እንደ ወጣ አየ፥ ዳዊትም በዚፍ ምድረ በዳ በጥሻው ውስጥ ይኖር ነበር።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 23:15
7 交叉引用  

የኢያቡስቴንም ራስ በኬብሮን ለነበረው ለንጉሥ ዳዊት ካቀረቡ በኋላ እንዲህ አሉ፤ “ሊገድልህ ይመኝ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ፤ ንጉሥ ሆይ፥ ዛሬ በሳኦልና በቤተሰቡ ላይ እግዚአብሔር ለጌታዬ ለንጉሡ ተበቅሎለታል።”


ያ ሰው የሚመስለው መልአክ እንደገና በዳሰሰኝ ጊዜ ብርታት አገኘሁ።


በበረሓ፥ በተራራ፥ በምድር ውስጥ ባሉ ዋሻዎችና ፈፋዎች ዞሩ። በዚህም ዐይነት ዓለም ለእነርሱ ተገቢ ስፍራ ሆና አልተገኘችም።


ዳዊት በዚፍ አጠገብ ባለው ምድረ በዳ ውስጥ በኮረብታማው አገር ተሸሽጎ ኖረ፤ ሳኦልም እርሱን ለማግኘት ዘወትር ይፈልገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ዳዊትን ለሳኦል አሳልፎ አልሰጠውም፤


የሳኦል ልጅ ዮናታንም እዚያው ድረስ ወደ ዳዊት ሄዶ እግዚአብሔር በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቀው መሆኑን በመግለጥ እንዲህ እያለ አበረታታው፤


ነገር ግን የዳዊት ተከታዮች “በዚህ በይሁዳ ስንኖር የምንፈራው ብዙ ነገር አለ፤ አሁን ደግሞ ወደ ቀዒላ ሄደን በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ላይ አደጋ ብንጥል ችግራችን የባሰ ችግር ይገጥመናል!” አሉት።


ሳኦል በሐኪላ ተራራ ላይ በሚገኘው መንገድ አጠገብ በሔሲሞን ፊት ለፊት ሰፈረ፤ ዳዊትም በምድረ በዳ ነበር፤ ሳኦል እርሱን ለመፈለግ መምጣቱን ባየ ጊዜ፥


跟着我们:

广告


广告